Wednesday, December 2, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


በጎንደር ከተማ በትናንትናው ዕለት በደረሰው የህወሓት ግዙፍ ወህኒ የእሳት ቃጠሎ ምክንያት በህወሓት መከላከያ ሰራዊት በተፈፀመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የሞቱ ሰዎች ቁጥራቸው እጅግ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ በታማኝ ምንጮች ተረጋግጧል፡፡ ከተጨፈጨፉት እልፍ አዕላፍ ወገኖቻችን መካከል ማንነታቸው የተለየው ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ትናንትና ማክሰኞ ዕለት ህዳር 21 2008 ዓ.ም በጎንደሩ የህወሓት ግዙፍ ወህኒ /ባህታ እስር ቤት/ የተነሳው ከባድ የእሳት ቃጠሎ የጀመረው ከረፋዱ ወደ አራት ሰዓት ገደማ ነው፡፡ በመሆኑም የህወሓት አገዛዝ ታማኝ ጦሩን ከሁመራና አካባቢው ጭኖ በፍጥነት ወደ ጎንደር ከተማ በማጓጓዝ እስረኞችንና ሰላማዊ ነዋሪዎችን በጥይት ጨፍጭፏቸዋል፡፡ የተጨፈጨፉት ሰዎች ቁጥራቸው የትየለሌ እንደሆነና ከመጠን በላይ የሆነ አስከሬን በአንድ ላይ ተከማችቶ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያረጋግጣል፡፡
ከተጨፈጨፉት እጅግ በጣም በርካታ ሰዎች መካከል ማንነታቸው የተለዩት ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ሲፈፀም ውሏል፡፡ አቶ አዱኛ የተባለው ሟች ዛሬ ከሰዓት በፊት በወገራ ወረዳ ገደብዬ ከተማ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተቀብሯል፡፡
የጎንደር ህዝብ በህወሓት አገዛዝ ላይ ከመቸውም ጊዜ በላይ ጥርሱን ነግሷል፡፡ ስለሆነም በጎንደርና አካባቢው ከፍተኛ ውጥረት አይሏል፡፡

No comments:

Post a Comment