በኦሮሚያ ክልል በኢሊባቡር ዞን ጉሬ ከተማ ከትግራይ ክልል መጥተው ነዋሪ የነበሩት አቶ ብርሃኔ ወልደጊዪርጊስ ወደ ኦሮሚያ ያቀኑት ከኢህአዴግ በፊት በነበረው ስርአት ነው፡፡
አቶ ብርሃኔም እንደማንኛውም ኢትዪጲያዊ ከኦሮሞ ተወላጆች ጋር እየነገዱ ይኖሩ የነበሩ ግለሰብ ናቸው፡፡ ግለሰቡ አይሱዙ የጭነት መኪና በገዙ ሰአት ንብረታቸውን የሚጠብቅላቸው ገንዘብ የሚቆጣጥርላቸው የቅርብ ሰው በማስፈልጉ የሚስታቸው ወ.ሮ አበባን ወንድም የሆነውን አቶ አለም ፍጹምን ከትግራይ የገጠር ክፍል ወደ ጎሬ ያስመጡታል፣ አቶ አለም ፍጹምም ኢሊባቡር ዞን ጎሬ ከተማ ከመጡ በሁላ በአይሱዚ መኪና ረዳትነት ስራቸውን ቀጠሉ ይህም በ1985 -1989 ባለው ገደማ አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ ከዚያ በሁላ አቶ ብርሃነ ወልደጊዪርጊስ ከነ ባለቤታቸው በአሁኔ ጊዜ በህይዎት የሉም።
የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ኦቶ አለም ፍጹም ከአይሱዙ መኪና ረዳትነት ወደ ድንገታዊ ባለሃብትነት ያደጉበት ሚስጥር በኢሊባቡር ዞን ጎሬ ለሚያውቋቸው ሰዎች እጅግ አስገራሚ እና አስደናግጭ ሁኗል፡፡
አቶ አለም ፍጹም ከስርአቱ ሰዎች ጋር በፈጠሩት ቁርኝት ድንገታዊ ሀብት መመንደጋቸውን ቀጠሉ፡፡
አለም ገነት የሚል የቤት ክዳን ቆርቆሮ ፋብሪካ ባለቤት ናቸው፣ የብረታብረት ፋብሪካ እና የሶፍት ወረቀት ማምረቻ ለቡ ኢንዱስቱሪ ዞን የሚገኙ ናቸው፣ የተለያዩ ድርጅቶችም አሏቸው።
በመጨረሻም በቀለበት መንገድ ሃና ማሪያም አደባባይ አካባቢ የሚገኘውን ሪቬራ ሆቴል የተባለውን ገነቡ፡፡ ከዚያ የህወሃት ድርጅት የሆነው መከላከያ ኢንጅነሪንግ እጅግ በጣም በተጋነነ ከመጋነነም በላይ ከፍተኛ በሆነ ዋጋ ሪቨራ ሆቴልን ገዛቸው፡፡ ከዚያም ፊላሚንጎ ቦሌ መንገድ ላይ ለአዲስ ሆቴል ግንባታ የሚሆን ቦታ ተሰጣቸው ድሬ ትዩብ ስለ አዲሱ ሆቴል ስለሚሰራው ተከታዩን መረጃ በፎቶ አስደግፎ አውጥዋል።
2.5 ቢሊዮን ብር የሚፈጅ ሆቴል በመዲናችን አዲስ አበባ እየተገነባ ነው!
ሆቴሉ ከአፍሪካ ቀዳሚው ያደርገዋል! (በተሻገር ጣሰው)
በአለም ገነት ንግድና ኢንዱስትሪ የሚመራው በመዲናችን አዲስ አበባ ፍላሚንጎ አካባቢ ባለ አምስት ሆቴልና ከአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርገው ሆቴል እየተገነባ መሆኑን የሆቴሉ ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አለም ፍፁም ለጋዜጠኞች በሸራተን አዲስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ::
ሆቴሉ ባለ 27 ፎቅ ህንፃ ሲሆን 500 ዘመናዊ ክፍሎች 10ሊፍቶች እንደሚኖሩትም የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ሆቴሉ 30 ከመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በአይነቱ ልዩ የሆነናና ከሁለት አመት በሆላ ስራው ሲጠናቀቅ ለ1ሺህ 500 ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር አቶ አለም ተናግረዋል::
——
የሚገርመው እና የሚደንቀው ነገር የትላንቱ የአይሱዙ መኪና ረዳት የዛሬው ቢሊየነር መሆን በቅርበት ለሚያውቋቸው የኢሊባቡር ጎሬ ነዋሪዎች አስደንጋጭ ሁንዋል፡፡ ይህን ጉዳዩ የአካባቢውን ተወላጆች በመጠየቅ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ከአቶ አለም ጀርባ ያለው የህወሃት ባለስልጣን ማነው እንዲሁም ይህን ሁሉ ሀብት እንዲሸከሙስ ማን ሰጣቸው የሚለው ጊዜ የሚፈታው እንቆቁልሽ ነው፡፡
በጣም የሚያስገርመው ነገር ያኔ በረዳትነት ሲሰረባቸው የነበሩት አማቹ አቶ ብርሃነ ከነ ባለቤታቸው ወ.ሮ አበባ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አሳዛኙ ነገር ከትግራይ ከገጠር አምተውተት በረዳትነት ሲሰራ ቆይቶ አሁን ድንገት ቢሊየነር የሆነው አቶ አለም ፍጹም የአቶ ብርሃነ ልጆችን እንኳን የማይረዳ መሆኑ ነው።
በአሁኑ ሰአት ገበሬዎችን በማፈናቀል እየገደለ የሚገኘው ህወሃት ለነደዚህ ያሉ ግለሰቦችን መኪና ረዳትነት ከሚሊየነርም አሻግሮ ወደ ቢሊየነር ወርውሮ ሚሊየን ዜጎችን ችግረኛ ማድረግ ነው።
No comments:
Post a Comment