Saturday, December 5, 2015

Abebe Gellaw
የህወሃቶች የአፓርታይድ ስርአት ከስር መሰረቱ ተንዶ እስካልወደቀ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍዳና ሰቆቃ ይቀጥላል። ስርአቱ የተመሰረተው በፋሺስታዊ አይዲዎሎጂ ላይ ስለሆነ በምንም አይነት መንገድ የመብት ጥያቄ ሊያስተናግድ አይችልም። ገበሬዎችን እና ምስኪን የከተማ ነዋሪዎችን የማፈናቀል ተግባራቸውም የስርአቱ ፋሺስታዊነት አንዱ መገለጫ በመሆኑ ከዚህ እኩይ ተግባራቸው የቆጠባሉ ብሎ ማመምን የዋህነት ነው። ስለዚህም ነው የዚህን ስርአት እድሜ ለማሳጣር ለስር ነቀል ለውጥ በአንድነት መታገል ወሳኝ የሆነው።
ትግሉ በጨቋኞች እና በተጨቋኞች፣ በፋሺስታዊ ስርአትና የስርአቱ ሰለባ በሆነው ኢትዮጵያዊ መካከል ስልሆነ መስመሩ ግልጽ ሆኖ ተሰምሯል። 
የህወሃቶችን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ለማምከን ሁላችንም በያለንበት በጭቁኑ ኢትዮጵያዊ መካከል መተማመ ለምፍጠር የድርሻችንን እንወጣ። 
ይህ ትግል በህዝቦች መካከል የሚደረግ ትግል አይደለም። ትግሉ በጨቋኝ ስርአትና በጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል የሚደረግ ትግል ነው።የጥቂት ዘረኞችን ስርአት በዘረኝነት ፈጽሞ መታገል አይቻልም። 
በዚህ አጋጣሚ ዘረኛና ከፋፋይ የሆኑ ጹሁፎችን የሚያሰራጩቱት በዋነኛነት ህወሃትና ሎሌዎቹ መሆናቸውን ከግንዛቤ በማስገባት ጎጂ ከሆኑ የቃላትና የምስል ልውውጦች መቆጠብ አጅግ ወሳኝ ነው። በንቃትና በአንድነት እምቢ አሻፈረኝ የሚል ህዝብ ፈጽሞ ሊጨቆን አይችለም።

No comments:

Post a Comment