(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
#በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በተነሳው የተማሪዎች አመፅና አለመረጋጋት ምክንያት መማር ማስተማሩ ሙሉ በሙሉ የሚስተጓጎልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑ ታወቀ፡፡
====================================================
በኦሮምያ እየተፋፋመ የሚገኘውን የህዝብ አመፅና ቁጣ ተከትሎ በሁሉም የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሁከት የነገሰ ሲሆን የህወሓት አገዛዝ የአግአዚ ኮማንዶን ጨምሮ ጦሩን በየዩኒቨርሲቲ ግቢዎች በማሰማራት የተማሪዎችን የተቃውሞ እንቅስቃሴ በኃይል ለመደፍጠጥ እየጣረ ይገኛል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በህወሓት ጦር ተወሮ ጥቁር ልብስ የለበሱ ተማሪዎች ከመንስ ቤት ሳይቀር እየተለቀሙ ወደ እስር ቤት በመጋዝ ላይ ናቸው፡፡
ወላይታ ሶዶ፣ ጎፋ ሳውላና ዳውሮ ዩኒቨርሲቲዎች በቅልብ ፌደራል ፖሊስ መሳሪያ አፈሙዝ ቁጥጥር ስር ወድቀው ሙሉ በሙሉ በአለመረጋጋት ጥልቅ ባህር ውስጥ ሰጥመዋል፡፡
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጦር ሰራዊት የመሸገበትን ግቢ እየለቀቁ በአቅራቢያቸው በሚገኘው ጫካ ውስጥ ገብተው ተጠልለዋል፡፡
No comments:
Post a Comment