Thursday, December 3, 2015

የወገኖቻችን ስቃይ፣ ችግርና ብሶት በያለንበት ይሰማን

የወገኖቻችን12144768_1617433048508870_4824757903625493537_n ስቃይ፣ ችግርና ብሶት በያለንበት ይሰማን
ኢትዮጵያነት ሲጠራ የሚያንገሸግሻቸው የወንበዴው ቡድን በዘርና በጎጥ ህዝብን ከፋፍለው የስልጣን ወንበራቸውን ዕድሜ ለማስረዘም ሌት ተቀን የሚቅበዘበዙት እራሳቸውን የትግራይ ነጻ አውጭ ነን ብለው በመሰየም የራሳቸውን የትግል ጓዶች ከማሃላቸው በመግደልና በማባረር ጥቂት የሚባሉ ቡድኖች ሀገሪቱን ለመምራት በለስ ቀንቷቸው፡ ይሄው 24 ዓመት መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ሲያሰኛው ጦርነት በመጫር 60 ሺ ያላነሰ ኢትዮጵያዊያንን ባላመኑት ጦርነት በመማገድ ህዝቡ እርስ በርስ እንዳይግባባ በዘርና በቋንቋ በአካባቢ በመገደብ፡ ከአንዱ አካባቢ ወደ ሌላው ሄዶ የመኖር መብቱን በመገደብ ይህ ነው የማይባሉ በደሎችን በዜጎች ላይ የመግደልና የማሰር አልፎም ተርፎ ለስደት በመዳረግ ሀገሪቱን የግላቸው በማድረግ የሀገሪታን አንጡራ ሃብቶች የግላቸውና ለድርጅታቸው በማዋል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይህ ነው የማይባል የመከራ ቀንበር ጭነውበት ሲቃይ ተቀባይ ሆኖ እንዲኖር አድርገውታል፡ ይህም አልበቃ ብሎቸው የውሸት ህገ መንግስት በመቅረጽ የአለምን ህብረተሰብ በማታለል ዜጎችን ለማፈኛ በማዋል ላይ ናቸው ።
ወንበዴዎቹ ይባስ ብለው ዜጎችን በጠራራ ጸሃይ በመግደል ላይ ነው፡ የዘረኛው የወንበዴው ጭቆና ያንገሸገሸው መሳሪያ በማንሳት በመታገል ላይ ሲሆኑ፡ ይህም ትግል ኢያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአገኘው አጋጣሚ ቢችል ትግሉን መቀላቀል ካልተቻለም ባለበት ቦታ ሆኖ ለነጻነት ታጋዮች መረጃ በመስጠት የትግሉ አጋር መሆን ይችላል፡ ይህ ትግል ለዲሞክራሲና ለነጻነት እኩልነት የሚደረግ ትግል ነው። ስለሆነ ማንኛውም ነጻነት ናፋቂ አቅሙ በፈቀደ መጠን የትግሉ አጋር መሆን ይቻላል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
ድል ለሰፊው ህዝብ !!

No comments:

Post a Comment