Wednesday, December 30, 2015

በዛሬዋ የወያኔው ኢትዮጵያ ውስጥ አማራን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን ሰው መሆንን እንጅ በጎሳ ማሰብን አይጠይቅም !!

በወልቃይት ሕብረተሰብ ላይ የሚደረገውን መንግሥታዊ ሽብር፥ የግፍ ግድያ፣ የጅምላ ጭፍጭፋና ዓፈና፥ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዜጎችን ማፈናቀል የወያኔ ሴራwelkayt
ከዛሬ 25 ዓመታት በፊት በነበረችው ኢትዮጵያ ሐገርነቷ የዜጎቿ የራሳቸው ሐብት ስለነበረች ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ግዛት ተዘዋውረው የሚኖሩባትhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/49563 ፤ሐብትና ንብረት ያፈሩባት፤ ደስታንና መከራን የተጋሩባት፤ ተጋብተውና ተዋልደው ተተኪ ትውልድ የፈጠሩባት፤ ባሕልና ቋንንቋ የተለዋወጡባት፤ በእምነት የተሳሰሩባት በአጠቃላ የሰው ዘር ምንጭ የሆኑት ውህዳን ነገዶችና ጎሳወች ኢትዮጵያዊ ሆነው ለረጅም ዘመናት የኖረባት ታላቅና ታሪካዊት ሐገር ነበረች። በዚህ አይነት የህዝባችንና የሐገራችን የታሪክ ትውስታ ሲዘከር መዘንጋት የማይገባው የአማራው ውህዳዊ ኢትዮጵያዊነት አስተወፅኦ ነው።በዛሬዋ የወያኔው ኢትዮጵያ ውስጥ አማራን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን ሰው መሆንን እንጅ በጎሳ ማሰብን አይጠይቅም !! ከዛሬ 25 ዓመታት በፊት በነበረችው ኢትዮጵያ ሐገርነቷ የዜጎቿ የራሳቸው ሐብት ስለነበረች ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ግዛት ተዘዋውረው የሚኖሩባት ፤ሐብትና ንብረት ያፈሩባት፤ ደስታንና መከራን የተጋሩባት፤ ተጋብተውና ተዋልደው ተተኪ ትውልድ የፈጠሩባት፤ ባሕልና ቋንንቋ የተለዋወጡባት፤ በእምነት የተሳሰሩባት በአጠቃላ የሰው ዘር ምንጭ የሆኑት ውህዳን ነገዶችና ጎሳወች ኢትዮጵያዊ ሆነው ለረጅም ዘመናት የኖረባት ታላቅና ታሪካዊት ሐገር ነበረች። በዚህ አይነት የህዝባችንና የሐገራችን የታሪክ ትውስታ ሲዘከር መዘንጋት የማይገባው የአማራው ውህዳዊ ኢትዮጵያዊነት አስተወፅኦ ነው። የአማራው ውህድ ኢትዮጵያዊነት፤-በመሰረቱ አማራ የተባለው ነገድ በማንኛውም ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቀው ምስራቅ አፍሪካዊት ሐገር ውሰጥ ከመሐል እስከ ዳር (ጠረፍ) ከሌሎች ነገዶች ጋር አብሮ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለረጅም ዘመናት የኖረ የህብረተሰቡ ክፍል ነው። አማራ በምስራቅ የሐገሪቱ ግዛት ከአፋር፣ ከኢሳ፣ ከሱማሌ፤ከሃደሬና ከኦሮሞ ጋር ተቀላቅሎ ምስራቃዊ ግዘትን አስከብሮና ባለቤት ሆኖ ከኖረው ሕዝባችን ውስጥ አነዱ ነው
። የሐገራችን ሰሜናዊ ግዘትም አማራው ከትግሬ፤ ከአፋር፤ ከኩናማ ከአገው፤ከቅማንት፤ከወይጦ ጋር ተቀላቅሎ ሰሜናዊ የሀገሪቱን ግዝት በማስከበር ባለቤት ሆኖ መኖሩን እነዚሁ አብረውት የኖሩት ወገኖቹ ምስክር ናቸው። በምዕራባዊ የሐገሪቱ ግዝትም አማራው ከአገው፤ ከጉምዝ፤ ከወይጦ፤ ከሺናሻ፤ ከበርታ፤ ከሻንቅላ፤ ከኑየር፤ ከአኘዋክ፣ከኦረሞ፤ ጎሳወች ጋር ተደባለቆ ምዕራባዊውን የሐገራችን ግዛት አስጠብቀውና ባለቤት ሆኖ የኖረ ነው። በሐገሪቱ ደቡባዊና ማዕከላዊ ግዛት ደግሞ ከጉራጌው፤ ከከንባታው፤ ከሐድያው፤ ከሲዳማው ከዶርዜው፤ ከኦሮሞው፤ከሰለጢው ወዘተ…ጋር ተቀላቅሎ አዲሰ አበባን ጨምሮ ኢትዮጵያዊ የሆነ ማሕበረሰብን በመፍጠር ቅለቅሉን ለመለየት በማይቻልበት መንገድ ውህድ ሆኖ ኖሮል። በዚሁ መሰረት፤- በእምነት፤በቋንቋ፤በስነምግባር፤ በመልካዓ ምድር የተዋሃደ ነው። የአማራው እምነት፤- ምንም እንኳን እምነት የግል አገር የጋራ መሆኑን ቢያውቅም አማራው በተፈጠረባቸው አካባቢወች ሁሉ በካባቢው ከሚገኙት ጎሳወች ጋር የተለያዩ እምነቶችን ተጋርቶ ፈጣሪውን ያመልካል። በጋራ ከሚጠቀምባችውም እምነቶች ውስጥ ኦርቶዶክሰ ተዋህዶ፣ እስልምና፤ ካቶሊክ፤ አደቨነቲሰት ሚሺን፤ ፐሮቲሰታንት የመሳሰሉት አማራው ከሚምንባቸው እምነቶች ውስጥ በምሳሌነት ይጠቀሳሉ። አማራው ማንኛውንም ሰው በሰውነቱ ከሚሰጠው ከበሬታ በተጨማሪ በሐይማኖቱ ከሌሎቹ ጎሳወች ጋር የተዋሐደበት ወገናዊ መግለጫው ለመሆኑ ማስረጃ ማጣቀስን የሚጠይቅ አይመስለኝም የነበረ- ያለና ወደፊትም የሚኖር እውነት ነው። የአማራው ቋንቋወች፤-የአማራ ነገድ ማንኛውንም ቋንቋ የሚጠቀምበት በመግባቢያነቱ ነው። ስለሆነም አማረኛ ቋንቋን ነገዱ በብዘት በመግባቢያነቱ ይጠቀምበታል ቋንቋው የሐገሪቱ የስራ ቋንቋ ስለሆነ አማራውም የስራ ቋንቋው አድርጎ ይሰራበታል። አማራው ማንኛውንም ቋንቋ የሚያው በመግባቢያነቱ እንጅ ለፖለቲካዊ ዘረኝነት መሳሪያ አድርጎ አይጠቀምም አማረኛ ቋንቋን የኔ ነው ብሎ የባለቤትነት ጥያቄ ጠይቆ አያውቅም አብረውት የኖሩትን ጎሳወች ቋንቋ ለመጋራት ከመጣር ውጭ የወገኖቹን ቋንቋ አጣጥሎ ወይም ለእድገታቸው መሰናክል ሆኖ የታይበት ወቅትም አልነበረም ለዚህም ነው አማራው በተወለደባቸው ቦታወች ሁሉ ከአማረኛ ውጭ ትግረኛን፤ አገውኛን፤አፋረኛን ሱማሊኛን፤ኦሮምኛን ጉራግኛን በመግባቢያነት ስለሚጠቀምባቸው እነዚህኑ ቋንቋወች የራሱ በማድረግ ጥቂት የማይባል የአማራ ነገድ አቀላጥፎ ይናገራል ይግባባባቸዋል። እንዲያው ለነገሩ ነው እንጅ አማረኛ ቋንቋን በየዘመናቱ የነገሱ ገዝወች ግዛታቸውን በሕዝቡ ውስጥ ለማስረፅ መግባቢያ ሆኖ እንዲገለግላቸው ተጠቀሙበትና አሳደጉት እንጅ የአማራ ሕዝብ የቋነቋው ባለቤት ሆኖ እንዲያድግለትና እንዲስፋፋለት የጠየቀበትም ሆነ የዚሕ ቋንቋ ብቸኛ ባለቤት ነኝ ያለበት አንድም የታሪክ አጋጣሚ አለነበረም። ስለዚሕ አማራው አማረኛን የሚያውቀው ውሕድ ሆኖ የመላው አትዮጵያ ሕዝብ መገልገያ ቋንቋ መሆኑንና በዓለም የቋንቋወች መስፈርት መሰረት አፍሪካ ውስጥ መስፈረቱን አሟልቶ የተገኝ ብቸኛ አፍሪካዊ ቋንቋ መሆኑን ነው። የአማራው ስነ - ምግባር፤- ሕዝብ እንደ ሕዝብነቱ ክቡር ነው የአማራው ማሕበረሰብ ይህን የሰው ልጅ መለያ ባሕርይ ጠንቅቆ በመረዳት ሰውን በሰውነቱ አክባሪ እንግዳ ተቀባይ አገሩን ወዳድና ፍፁም ስላማዊ ሕዝብ ነው አብረውት የኖሩት ወገኖቹ (ጎሳወች) ይመሰክሩለታል። አማራው ፍቅርን መረዳዳትን መጋባትና መዋለድን ያውቅበታል። በየትኛውም የሀገሪቱ ግዛቶች አብረወት ከሚኖሮት ጎሳወች ጋር በጋብቻ ለመተሳሰሩ ለረጅም ዘመናት ያዳበረው የተዋልዶ ታሪኩ ሕያው ምስክር ነው። ዛሬ ከአማራው ጋር አልተዋለድንም አልተዛመድንም ንፁሕ ዘር ነን የሚሉት ወያኔና ወያኔ የወለዳቸው ዘረኞች ናቸው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን እንደሕዝብነቱ እንዲሕ ያለ ችግር እንደለለበት የተረጋገጠ ነው። እንዲያውም አንዳንድ የወያኔና የኦነግ መሪወች ሚስቶቻቸው ወይ ባሎቻቸው የአማራው ነገድ መሆናቸውን እያወቁ ስለዘር ጥራት ይሰብካሉ አማራውን ይጠላሉ ያስጠላሉ። ነገር ግን ትዝብት ካልሆነ በስተቀር የአማራውን የጋብቻ ባሕል ፈፅሞ የሚለውጡት አይደለም ምክንያተም አማራው እንደሕዝብነቱ እራሱን በዘር ቡድን አደራጅቶ በማንኛውም ጎሳ ላይ ሳንጃ መዞ ሰው የገደለበት፤ የማንንም ንበረት የዘረፈበት፤ ስለ-ዘር ጥራት የቀሰቀሰበት፤ የታሪክ ክሕደትና ስህተት የፈፀመበት አጋጣሚ ፈፅሞ የለም ወደፊትም አይኖርም። እንግዲህ ከዚህ በላይ ስለአማራው ውህድነትና ከ 25 አመታት በፊት በነበረችው ኢትዮጵያ የአማራውን ሐገራዊ ተሳትፎ በትንሹም ቢሆን ለማመላከት ሞክሬለሁ። የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የማናት ? የአማራው እጣ ፈንታስ ምን ይመስላል ? የሚሉትን ማየቱ ተገቢ ይመስለኛል። በዛሬይቱ የወያኔው ኢትዮጵያና የአማራው እጣ -ፈንታ የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን በፈፀሙት ፀረ-ኢትዮጵያ ሴራ ወያኔ የዛሬ 25 ዓመት ጀምሮ በለስ ቀንቶት የምኒልክን ቤተመንግስት ወሮ ስልጣን ለመቆናጠጥ በቅቶል። የሕዝቡን ሐገራዊ ባለቤትነት በሐይል ቀምቶ ያለሕዝቡ ፈቃድ ኢትዮጵያን እንደግል ሐብቱ በመቁጠር እንዳሻው የሚሸነሸናት የሚሸጣትና የሚይለውጣት አገር የዛሬዋ የወያኔው ኢትዮጵያ ናት። የትገሬ ነፃ አውጭ ቡድን የህዝባችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር፤ የአብሮነት ታሪክ፤ ባሕሉንና እምነቱን ሁሉ በማጥፋትና በማፈራረስ አሁን ለደረሰበት ወያኔዊ ድል የተመቻቸችና ታሪክዊ ክሕደት የተፈፀባት የወያኔው አገር ሆናለች። ወያኔው ዘራፊና ነፍሰገዳይ አገዛዙን በማስፋት የዜጎችን ደም መጥጦ አጥነታቸውን በሚሰባብረው ጥርሱ፤ እሳት ጭብጦ እሳት በሚወረውረው መዳፉ አሰገብቶ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለውን ትወልድ ሁሉ እያደቀቀና እያቃጠላቸው ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ከዓለማችን ውስጥ ጊዜ የከዳት ወዳጅ የሌላት ባአጥፍቶ ጠፊወች የተከበበች ሐገር ናት። በዛሬዋ ኢትዮጵያ ዜጎች በሲኦል እጅ ወድቀው ለአስከፊ እልቂት የተዳረጉባት ህግ አልባዋና የነፃነት ሰንደቅ የማይታወቅባት ኢትዮጵያ ናት ። ዛሬ አማራው በኢትዮጵያዊነት እምነቱ ብቻ እንደ ወንጀለኛ ተፈርጆ የመጀመሪያ የጥፋት ሰለባ ሁኖ የዘር ማጥፋት ወነጀል የተፈፀመባትና የሚፈፅምባት ኢትዮጵያ ነው ያለችው። አማራውን የማጥፋቱ ስራ የወያኔው የመጀመሪያ ፐሮገራሙ ስለሆነ አልሞና አቅዶ ዘምቶበታል። የትገሬ ነፃአውጭ ግንባር የተባለው ጭራቅ ባምሳሉ የፈጠራቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች በማሳደም አማራውን ያለ አንዳች ምክንያት ሰባዊ ተፈጠረሮውን ገፈው ፈፅሞ ከኢትዮጵያ ምድር እያጠፉት ነው። በ ኤርትራ፤በትገራይ፤በሐረር፤በጅጅጋ፤በቀላፎ፤በበደኖ፣ በአርባጉጉ፣ በነቀምት፣ጊዳብ ሺራቦ፣ በአሰቦት፣በባሌ፣ በአርሴ ፣ በቦረና፣ በጅማ፣ በኢሉባቦር፣በወተር፣ በባሕርዳር በደብረ ማርቆስ፤ በቤንሻንጉል፣ በጉራ ፈርዳ፣ በሰሜን ጎንደር፤ በወልቃይት፣ በጠገዳ፤ በደሴ፤በራያ፤በቆቦ፤በደቡብ ጎንድር…. ወዘተ የተካሄደውን የአማሮች ጭፍጨፋ የማያውቅ የኔ ዘመን ትውልድ ስለሌለ ለቀባሪ አረዱት እንዳይሆንብኝ በትህትና እጠይቃለሁ። ወያኔ ከደደቢት ወጥቶ ወደ ወሎ ጎንደር፤ ጎጃምና ሸዋ ግዛቶች በተስፋፋበት ወቅት የገበሬውን መሬት ፤የቤት እንሰሳት፤እህል ዘርፎል። በነዚሁ ክ/ሐገራት የሕክምና፣የትምህርት፤የባሕል፤ የግበርናና አገልግሎት ሰጭ መንግስታዊ ተቋማትና የግል ድርጅቶች ተመዝብረዋል ተቃጥለወል ወደትግራይ ተነቃቅለው ተጓጉዘዋል ዛሬም ቀጥሎል። የተለያዩ የግዞትና ማጎሪያ በታወችን በማቋቋም የአማራውን ህዝብ በጫካ፡ በዋሻ፤ከመሬት በታች ተቆፍሮ በተዘጋጀ ጉድጓድ በገፍ አስሮል አሰቃይቶል አሁንም እየተሰቃየ ነው።በአንድ ስር ቤት ውስጥ 4000-5000 ሰው ያላንዳች ፍትህ ታጉሮል ዛሬም እየታጎረ ነው። አማራው በማጎሪያው ቦታወች ድብደባ የተፈፀመት ሲሆን በመኖሪያ ቤቱም ከልጁቹና ከቤተሰቡ መካከል ስብናውን በሚያዋርድ መንገድ ተደብድቦል፤ በኤሊክትሪክ ንዝረት ተጠብሶል፣ በቀዝቃዛ ውሐ ተነክሮል የፍጥኝ ታስሮ ተዘቅዝቆ ደም እየተፋ ጥፍሩ ተነቅሎ እፍረተ ስጋው ተሰልቦል። በድብደባው ብዛት ሕይወቱ ያለፈው አካለ ጎደሎ የሆነው አማራ በሺሕ የሚቆጠር ስለሆነ በእማኝነት ለማቅረብ የሚከብድ አይደለም። አማራው የሚፈፀምበት ግድያ በ 4 የተከፈለ ነው አንደኛው የጅምላ ፍጅት ሲሆን በሜዳ፤ በጫካና በገድል በሰልፍ አሰልፎ ባልሞ ተኳሺች የጥይት ሩምታ ስንት ጣልክ እየተባባለ የተፈፀመ እልቂትና በአንድ ጉደጓድ እስከ 400 እሬሳ የተቀበረበት ነው። ሁለተኛው ከእስር ቤት ተሰቃይቶ መጨረሻ የሚገደልና ሲቀበር ታሞ እንደሞተ በማስመሰል የሚነገር ነው። ሶስተኛው ግድያ በመሰወር የተያዘና በግፍ አገዳደል ተገሎ የሰውነት አካላቱ ተቆራርጦ በጆንያ ተጠቅሎ የሚቀበር ወይም በጦር ተወግቶ፤በቢልዋ ታርዶ ገደል የሚወረወርና እሬሳው በእሳት የተቃጠለ ነው። የተገደሉ እናት ነፍሰጡሮች ሆዳቸው ተቀዶ ፅንሱ ወጥቶ ለውሻ ተወርውሮል ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሕፃናም አነገታቸው እየተቀላ በግፍ አገዳደሉ ውስጥ ይገኙበታል። አራተኛው ግድያ አገር ሰላም ነው ብሎ በቤቱ ውስጥ በተኛበት ሌሊት ከነንብረቱና ከልጆቹ በእሳት ተለብልቦ የተገደለ ነው። በአማራው ላይ የተጠናና ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ የተደረገ ማህበረዊ ቀውስ እንዲገባ ተደርጎል። ገጠሬው ወይም ገበሬው ተወልዶ ባደገበት በየትኛውም ኢትዮጵያ ክልል እንዲፈናቀል በማድረግ አገር የልሺ ስሜት እዲሰማው ከመሆኑም በላይ ንብረቱን ተዘርፎ ንብረት የሌለው ደሃ ለማኘ አድርገውታል፤ ቤተሰቡን መምራት ባለመቻሉ ልጆቹ ተበትነው ለስደትና ለውቅያኖስ አሳ ቀለብ ሆኖል። ሴት ልጆቹ በወያኔ ደላላወች ለወሴብ ንግድ ገቢያ ላይ ውለው ኩሩ ባሕሉን መሳቂያና መሳለቂ አደርገውታል።ኤች አይቪ፤ ወባ፤ ካንሰር፣ስራ አጥነት፣የጭንቀትና የአእምሮ በሺታ...ወዘተ የተለያዩ ተላላፊ በሺታወች እንዲጨርሱትና ትውልዱ ኢንዲጠፉ ሆን ተብሎ በወያኔ ሰራሺ መርዝ ተነስንሶበት እየተቃጠለ ነው። ከተሜው ነጋዴው ከንግዱ ምሁሩ ከመንግት ስራው ተፈናቅሎ የተሳካለት አገሩን ጥሎ ሲሰደድ ያልተሳካለት ደግሞ ህሊናው ተሸብቦ እንዳይናገር ተለጉሞ በቁሙ ሞቶ መኖር አይሉት ሞት እየኖረ የፈጣሪን ትግሰትና ቸርነት በመመኘት ወደሰማይ አንጋጦ ሲለምን ይወላል ያድራል። ባጠቃላይ በዛሬዋ የወያኔው ኢትዮጵያ አማራን የገደለ ይሾማል፤አማራን የዘረፈ ዲሞክራት ተብሎ ይወዳሳል፡ አማራአን ያፈናቀለ ለክብሩ መዳሊያ ይበረከትለታል፤ የአማራውን ባሕል ሐይማኖት ያራከሰና ያዋረደ የታሪክ ባለሞያ ሊቅ ይባላል፤አማራንው እንደ እንሰሳ አሳዶ ማጥፋት ሕጋዊ ሆኖ እየተሰራበት ስለሆነ አማራ ገዳይ ብሎ መፎከር ለወያኔና ለተላላኪወቹ እጅግ የሚስደስታቸወ እለታዊ መፈክር ነው። ወገን ሆይ !! አማራን ከፈፅሞ ጥፋት እናድን !!! በማጠቃለያየ ላይ ማለት የምፈልገው የትግሬ ወያኔና የተላላኪወቹ በሆነችው በዛሬዋ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራው ላይ እየተፈፀመ ያለው አማራንና ሐገሩን ፈፀሙ የማጥፋት እርምጃ ግልፅና የማያሻማ በአይን የሚታይ እውነታ ነው።ባንፃሩ ደግሞ የአማራው እልቂት የሚቆጫቸው የሌሎቹ ጎሳወች ተወላጅ ወገኖቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ ለአማራው ወገናቸው የሚያሳዩት ሰባዊነት ወገናዊነት የሚአበረታታ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ምስጋና የሚገባቸው ነው። ስለዚህ በዛሬዋ የወያኔው ኢትዮጵያ አማራውን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን ሰው መሆንን እንጅ በጎሳ ማሰብን አይጠይቅም። በትግሬ ነፃ አውጭና በተላላኪወቹ አማራው የገጠመውን ጨርሶ የመጥፋት አደጋ ሰው ሆኖ የተፈጠረ ወገኑ ሁሉ እንደራሱ ሰውነት በማየት አማራውን ከፈፅሞ ጥፋት ይታደገው ዘንድ ስብእናው ያስገድደዋል። የነገዱ ተወላጆችም ኢትዮጵያንና ነገዱን ከጨካኙ ወያኔና ተላላኪወቹ ጭፍጨፋና ዘረፋ የመታደጉ ሐላፊነት የጉሳ ጥያቄ ሳይሆን ሰው ሆኖ የተፈጠረውን አማራ እንደሰው የማዳን ነው። በዛሬዋ የወያኔው ኢትዮጵያ የአማራው ህልውና እንደሰው መኖር ወይም ያለመኖር ጥያቄ ውስጥ የገባ መሆኑን በመረዳት የአማራው ልጆች በያሉበት ቦታ ሁሉ በአፋጣኝ ተደራጅተው ማንኛውንም የትግል ስልት ተጠቅመው ወያኔና ተላላኪወቹ በአማራው ላይ የሚፈፅሙትን አጥፍቶ የመጥፋት አደገኛ አሸባሪነት ሊመክቱ ይገባቸዋል ብየ አመናለሁ ይህ ሳይሆን ቢቀር የታሪክና የትውልድ ተጠያቂነት ፈተና በራሳችን ላይ እያንዣበበ መሆኑል ልንገነዘብ ይገባል። ድል ለሕዝባችን !! ሞት ለወያኔና ተላላኪወቹ !! መሰረት ቀለመወርቅ

No comments:

Post a Comment