በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በተነሳ የተማሪዎች ተቃውሞ የፌደራል ፖሊስ ግቢ ውስጥ ገብቶ በርካታ ተማሪዎችን በሰደፍ እና በዱላ ሲቀጠቅጥ ነበር:: ከፖሊስ ጥይትና ዱላ ለማምለጥ ከ3ኛ ፎቅ የዘለሉ ተማሪዎችም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የሚመጡ መረጃዎች ያስታውቃሉ:: እስከሁን ከ40 የማያንሱ ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአይን እማኞች ሲገልጹ የሞቱት ቁጥር እስካሁን የታወቀው 3 ብቻ ነው::
የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም ተማሪዎቹ ባነሱት ተቃውሞ ከፍተኛ የሆነ መደናገጥ ውስጥ የገባው ሕወሓት የሚመራው መንግስት በፌደራል ፖሊሶች አማካኝነት ጉዳት ማድረሱን ቀጥሎበታል:: የተማሪዎቹ አመጽ በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች እየተንሰራፋ ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውጥረቱ እንዳየለ ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች አስታውቀዋል::
በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሆስፒታል – ፎቶዎች ይመልከቱ
No comments:
Post a Comment