Friday, November 27, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ‪#‎በጎንደር‬ ከተማ ቀበሌ 17 ሁለት ሰላማዊ ወጣቶች በህወሃት ልዩ ኃይል ጦር በጥይ ተደብድበው ተገደሉ፡፡ ‪#‎አንድ‬ የጠገዴ ታጣቂ ሁለት የህወሓት ፖሊሶችን ገድሎ በረሃ መውጣቱ ተዘገበ፡፡ ====================================================


በጎንደር ከተማ ቀበሌ 17 ሁለት ሰላማዊ ወጣቶች በህወሃት ልዩ ኃይል ጦር በጥይ ተደብድበው ተገደሉ፡፡
ህዳር 12 2008 ዓ.ም በጣት የሚቆጠሩ የቀበሌ 17 ወጣቶች መጥምቁ ዮሃንስ አካባቢ በቀሃ ወንዝ ዳር አቅራቢያ ተሰባስበው ህዳር ሚካኤልን በጋራ በማክበር ላይ እያሉ የህወሓት ልዩ ኃይል አባላት ደርሰው ወጣቶቹን ለመበተን ድንገት በከፈቱት ተኩስ ነው ሁለቱ ወጣቶች በግፍ የተገደሉት፡፡
በጥይት ከተደበደቡት ሁለቱ ወጣቶች መካከል አንደኛው ቶሎ ነብሱ ባለመውጣቱ ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ለህክምና ተወስዶ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ ህይወቱ ሲያልፍ የአካባቢው ነዋሪዎች ወጥተው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል አጥር ዙሪያ በጥበቃ ላይ በነበሩት ጥቂት የህወሓት ልዩ ኃይል ጦር አባላት ላይ ድብደባ በመፈፀም ቁጣቸውን የገለፁ ሲሆን የልዩ ሃይል ጦር አባላቱ ሮጠው ለጥቂት ከሞት አምልጠዋል፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግቢና አካባቢው ሌሊቱን ከፍተኛ ግርግር ተነስቶ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንዳደረ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
አንድ የጠገዴ ታጣቂ ሁለት የህወሓት ፖሊሶችን ገድሎ በረሃ መውጣቱ ተዘገበ፡፡
ህዳር 14 2008 ዓ.ም ክምሽቱ 2፡30 ላይ ሁለት ፖሊሶችን ተኩሶ በመግደል እንደታጠቀ አምልጦ ጫካ የገባው ታጣቂ ስሙ ሀጎስ ይሰኛል፡፡
በታጣቂው ሀጎስ እርምጃ የተወሰደባቸው የአገዛዙ ፖሊሶች ደግሞ ኮንስታብል አስቻልና ኮንስታብል አታለለ ይሰኛሉ፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)

No comments:

Post a Comment