Monday, November 30, 2015

ኢሳት ዜና


ተጨማሪ መረጃ ከሃሮማያ
ሁለት ተማሪዎች ከፌደራል ፖሊስ ዱላ ሲሸሹ ከ3ኛ ፎቅ ለመዝለል ሞክረው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ለህይወታቸው አስጊ እንደሆነ የሀረር የሆስፒታል ምንጮች ገልጸዋል። ከ30 በላይ ተማሪዎች ታፍሰው ወደ እስር ቤት የተወሰዱ ሲሆን በሃሮማያ ካምፓስ መንገድ ላይ የተገኘ ተማሪ ሁሉ በተመሳሳይ እየታሰረ ነው። ከመኝታ ክፍሉ ማምሻውን ያነጋገርነው ተማሪ ''..ለህይወቴ ሰግቼአለሁ። የኦሮሚያ ፈጥኖ ደራሽና የፌደራል ፖሊስ በር እየሰበሩ እየደበደቡ ናቸው። ሴቶችንም መኝታ ክፍላቸው ገብተው እየደበደቧቸው ነው። በጣም አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው።..'' ብሏል። ወደ ሀረርና ድሬዳዋ የሚያመልጡ ተማሪዎች ኬላ ላይ ተይዘው ወደ እስርቤት መወሰዳቸውም ታውቋል። የሃሮማያውን እንቅስቃሴ እየተከታተልን እንዘግባለን።.


No comments:

Post a Comment