Tuesday, November 10, 2015

በኢትዮጵያ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ የተነሳ በቆቦ ወረዳ አንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ብቻ በየቀኑ 2 ህፃናት ይሞታሉ * (ቢቢሲ በቆቦ አካባቢ ያለውን ድርቅ የዘገበበት http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48129ሳዛኝ ቪዲዮ ይዘናል) -

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ በተከሰተው ከባድ ድርቅ የተነሳ 15 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው አስታወቀ:: ድርጅቱ ባወጣው መግለጫውም በሃገሪቱ ሰሜናማው ክፍል ለዘገባ በተመረጠ ቦታ ብቻ በረሃብ የተነሳ (በቆቦ ወረዳ አንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ብቻ) በቀን 2 ህፃናት ሕይወታቸው እንደሚያልፍ አስታውቋል::
ዝናብ ባለመዝነቡ የተነሳ ሰብል ማምረት እንዳልተቻለ ያስታወቀው የተባበሩት መንግስታት የሚጠበቀውን ያህል ማምረት እንዳልተቻለ ጠቅሷል:: በዚህም መሠረት የተባበሩት መንግስታት በድርቁ የተነሳ የተጎዱትን ለመርዳት ከ330 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል::
ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያምም ሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቅርቡ በሰጧቸው ቃለምልልሶች በዚህ ረሃብ የሞተ ሰው የለም ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን ይህ የቢቢሲ ዘገባ ሁለቱንም ሚኒስተሮች እርቃናቸውን ያስቀረ እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ::
በ2016 መግቢያ ላይ ይህን ያህል ገንዘብ ኢትዮጵያውያኑን ለመመገብ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ሲያስቀምጥ ቢቢሲ በሰሜን ኢትዮጵያ በቆቦ አካባቢ ተዘዋውሮ ድርቁን እንደሚከተለው ዘግቦታል::


በኢትዮጵያ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ የተነሳ በቀን 2 ህፃናት ይሞታሉ * (ቢቢሲ በቆቦ አካባቢ ያለውን ድርቅ የዘገበበት አሳዛኝ ቪዲዮ ይዘናል)

-

No comments:

Post a Comment