ትግራይን ለማስገንጠል ነፍጥ አንስቶ የሸፈተው ህወሓት የደርግ ከህዝብ ተነጥሎ መዳከምና በወቅቱ ሌላ የታጠቀ ጠንካራ ተቀናቃኝ ኃይል አለመኖሩ የፈጠረለትን አጋጣሚ ተጠቅሞ ሀሳቡን በመቀየር መላ ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ የስልጣንና የምዝበራ አድማሱን ለማስፋት ሲያቅድ ከብሄር ፖለቲካ ጭቃ አምቦልቡሎ በአምሳሉ ከፈጠራቸው የጎሳ ድርጅቶች መካከል አንዱና ዋነኛው "ብሄረ አማራ ዴሞክሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን" እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡
ብአዴን የኢትዮጵያ አንድትን ከሚያራምደው ኢህአፓ ወጥቶ ከኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ኢህዴን በህወሓት ትዕዛዝ ወደ "ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ" ተለውጦ ወደ ዘር ፖለቲካ ሸለቆ ተወርውሮ በጭንቅላቱ ተተክሎ የቆመ እና የአማራው መጨቆኛ ዋነኛ መሳሪያ ነው፡፡
ብአዴን "በአማራ ተወላጆች የሚመራ የአማራ ድርጅት" እንደሆነ አስመስሎ በአማራው ህዝብ ፊት ለመታየት ይሞክር እንጂ ዋነኛና ተቀዳሚ ዓላማው አማራውን ማዳከምና ማግለል ነው፡፡
ብአዴን 35ኛ ዓመት የሎሌነት ዘመኑን የደፈነው በአማራ ተወላጆች እየተመራ አይደለም፡፡
•ታምራት ላይኔ የጉራጌ ተወላጅ
•በረከት ስምኦን (መብራህቶም ገ/ህይት) የኤርትራ ተወላጅ
•ህላዌ ዮሴፍ የኤርትራ ተወላጅ
•ተፈራ ዋልዋ የሲዳማ ተወላጅ
•አዲሱ ለገሰ የሀረር ተወላጅ...
ሌላም ብዙ መጠቃቀስ ይቻላል አጥንት ቆጠራ የህወሓትና የአሻንጉሊት ድርጅቶቹ የእነ ብአዴን ተግባር ስለሆነ ነው አንጂ፤ ብአዴን "የአማራ ድርጅት ነኝ" እያለ ደጋግሞ ስለሚነግረን በእነሱ የዘርና የቋንቋ ፖለቲካ ስሌት ዲስኩር ፈፅሞ አለመሆኑን በትንሹም ቢሆን ለማስረዳት ተሞከረ እንጂ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዘር ሃረጉ የተመዘዘበት ግንድ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ ቋንቋ ተፈጥሯዊ ስላልሆነ ፈፅሞ መለያ ሊሆን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያዊ ቋንቋውን አንደ ዘር መለያ ካልተጠቀመበት በስተቀር አጥንቱን ወደ ኋላ ቆጥሮ ደሙን በትክክል ሊናግ አይችልም፡፡
ነገር ግን "የአማራው ተወካይ ነኝ" የሚለን ብአዴን የአማራነትም ሆነ የኢትዮጵያዊነት ስነ-ልቦና ጨርሶ የለውም፤ የአማራም የኢትዮጵያም የለየለት ጠላት እንጂ፡፡
በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የሚልሱት የሚቀምሱት አጥተው በረሃብ እየተሰቃዩ ብአዴን በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ደፍቶ የ35 ዓመታት የሎሌነት ዘመኑን ሻምፓኝ በመራጨት እያከበረው ነው፡፡
ምንጊዜም ቢሆን እወክለዋለሁ የሚለው ህዝብ ቀንደኛ ጠላት የሆነው ብአዴን ለህወሓት እየተላላከ ግፍና በደል ሲፈፅም የኖረበትን ዘመኑን አሁንም ከግፍ ላይ ግፍ ደራርቦ በመስራት እያከበረው ይገኛል፡፡
ከብአዴን 35ኛ የሎሌነት ልደት ዘመን ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጌታው ህወሓት መከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይል ጦር የጎጃም፣ ወሎና ጎንደር ዋና ዋና ከተሞችን ወርሮ ህዝቡን መፈናፈኛ አሳጥቶት ይገኛል፡፡ በተለይም ትናንት ከዋዜማው ጀምሮ ህዝቡን በጠብመንጃ ማዋከቡና ማሸበሩ በእጅጉ በርትቷል፡፡
(አ.ታ ኦሮማይ)
No comments:
Post a Comment