የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወልቃይት ቀፍታ፣ አድ ኸርዲ፣ አፀ ሐርማዝ፣ አድ ፀፀርና በሌሎችም ትንንሽ ከተሞች በመዘዋወር ለሁለት ተከታታይ ሌሊቶች በራሪ ፅሁፎችን በተሳካ ሁኔታ ለህዝቡ አሰራጭቷል፡፡
የአረበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት አርብ ሌሊት በወልቃይት ቀፍታና አድኸርዲ የድርጅቱ ዓላማና የትግል ጥሪ የታተመባቸውን ወረቀቶች በገፍ ለህዝቡ አድርሷል፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በአፀ ኸርማዝና አድ ፀፀር በራሪ ፅሁፎችን ለህዝቡ የበተነው አሁን ያለፈው ቅዳሜ ሌሊት ነበር፡፡
በራሪ ፅሁፎቹ "እኛ አርበኞች ግንቦት 7 ነን!" የሚል ርዕስ አላቸው፤ "...እኛ ለነፃነትና ለፍትህ የቆምን፤ ለእኩልነትና ለአንድነት የተጋን፤ ለህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት እየደማንና እየሞትን የምንገኝ፤ የህዝብ ጭቆና እና ምሬት የወለደን አርበኞች ግንቦት 7 ነን..." የሚል ሀሳብም ይገኝበታል፡፡
በአራቱ ትንንሽ ከተሞችና በሌሎች መንደሮች በበራሪ ፅሑፎች መበተን በእጅጉ የተደናገጠውና የተረበሸው የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ ታጣቂ ኃይል በአካባቢው እያንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ የህወሓት መከላከያ ሰራዊት የጦር አዛዦች በጥልቅ የጭንቅ ባህር ውስጥ ሰጥመው ሰራዊቱን ከበረሃ በረሃ እያንከራተቱት ነው፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ወደ አይቀሬው ህወሓትን የመደምሰስ የመጨረሻ ፍልሚያ ሜዳ በፍጥነት እየተራመደ በመገስገስ ላይ ይገኛል፡፡ ሀወሓትም እንዲሁ ወደ ተማሰው መቃበሩ በፍጥነት እያመራ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment