በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የተቀሰቀሰውን የተማሪዎች አመጽ በተመለከተ መረጃዎች እየደረሱን ነው። ግቢው በፌደራል ፖሊስ ተወሯል። ወደ ዩኒቨርስቲው የሚወስዱት መንገዶች ተዘግተዋል። የፖሊስ ሃይል ተጨማሪ ወደ ግቢው እየተጠጋ ነው። በድሬዳዋ ካምፓስም በተመሳሳይ አመጽ ተቅስቅሷል። በርካታ ተማሪዎች ታስረዋል። በሌሎች ካምፓሶች ውጥረቱ እንደጀመረም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ለጊዜው ቁጥሩ ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቅም የተገደሉ ተማሪዎች እንዳሉ እየተነገረ ነው። ኢሳት በዚህ ዙሪያ ማጣራት እያደረገ ነው። በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ የተነሳው ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞችም ቀጥሏል። በዛሬው ኢሳት ሬዲዮ ዘገባ ይኖረናል።
No comments:
Post a Comment