Tuesday, November 17, 2015


በከፋተኛ ትምህረት
ተቛማት የሚማሩ ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲያቛርጡ በማስገደድ የገዢው የኢህአዴግ ስረአትን የሚከተለው ፓሊሲና እስትራተጂ እንዲሰለጥኑ እየተደረገ መሆኑን ተገለፀ።
በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአሁኑ ወቅት የከፋተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ያለፋላጎታቸውና እምነታቸው መደበኛ ትምህርታቸውን በማቋረጥ በስልጣን ላይ ያለው የገዢው ኢህአዴግ ስረአት የሚከተለው የለው የፖለቲካ አስተዳደርና ፖሊሲ እንዲቀበሉና ከኢህአዴግ በስተቀር ለሌላ እንዳይደጉፉና ለቀጣይ የአምስት አመት መርሃ ግብር ለማስረዳት በሚል በበላይ ባለ ሰልጣናት በሚመራ ጥብቅ ሰብሰባ ተጠምደው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው ተቃዋሚ ድርጅቶች ፖሊሲያቸውንና አላማቸውን ለከፍተኛ ትምህርት ተቛማት ተማሪዎች እንዲሁም ለታችኛው የኢለመንታሪና ሃይስኩል ተማሪዎች ጭምር ሰብሰባ አድረገው እንዳያስረዱ ተከልከለው እያሉ ኢህአዴግ ግን ስልጣኑን ተጠቅሞ መደበኛ ትምህርት ሳይቀር በማቋረጥ የድርጅቱን አቋምና አላማውን ለማስረዳት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ተቃውሞ እየቀርብበት መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment