Wednesday, November 25, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)


ሰሞኑን በወላይታ ሶዶ የተጀመረው የአርበኝነት ትግልን የሚያፋፍሙ ፅሁፎችንና ምስሎችን የያዙ ወረቀቶችን የመለጠፉ ተግባር አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በሙሉ በትግል ጥሪ ወረቀቶች ተጥለቅልቀዋል፡፡
"አንዳርጋቸው ፅጌ የጀመረውን ትግል እኛ እንጨርሳለን!" የሚልና ሌሎችን መፈክሮች ከምስል ጋር የያዙት ወረቀቶች በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳዎች ጎፋ ሳውላ፣ ቁጫ፣ ሰላም በር፣ ዳውሮና በሁሉም ቀበሌዎች በስፋት ተለጥፈዋል፡፡
በዚህ የተነሳ የአካባቢው የህወሓት ደህዴግ ሹሞች በከፍተኛ ጭንቀት በተሸበበ ስብሰባ ላይ ናቸው፡፡ በስብሰባው ላይ በደቡብ ኢትዮጵያ በተለይም በአርባ ምንጭና በወላይታ ሶዶ እየተቀጣጠለ የሚገኘው ህዝባዊ ትግል ከቁጥጥራቸው ወጥቶ ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ አምነዋል፡፡
የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ፖሊሶች በከተሞች የትግል ጥሪ ከያዙት ወረቀቶች በተጨማሪ የጦር መሳሪያም ተሰራጭቷል የሚል ስጋት አድሮባቸው ያለፈውን ሌሊት ሳይተኙ በከፍተኛ ጥበቃና ቤት ብርበራ አሳልፈውታል፡፡
በአጠቃላይ በአሁኗ ሰዓት በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳዎችና ልዩ ልዩ ቀበሌዎች ከፍተኛ ሽብር ነግሷል፡፡

No comments:

Post a Comment