(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
የወልቃይት ህዝብ ለነፃነቱ ሊታገል ከመቸውም ጊዜ በላይ ቆርጦ በአንድነት መነሳቱ ታወቀ፡፡
የወልቃይት ህዝብ ህወሓት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ ተደጋጋሚ ግፍና በደል ያደረሰበት በመሆኑ መቸም የማይፈታ ቂም አለው፡፡ ህወሓት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ደግሞ ሳይፈልግ ከጎንደር እንዲገነጠል ተደርጎ ወደ ትግራይ ክልል በመጠቃለሉ ሲያነሳው የቆየው ያልተመለሰ ጥያቄ አለው፡፡
ህወሓት የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የጀመረውን የነፃነት ትግል እንቅስቃሴ ጦር ኃይሉን ተጠቅሞ ለመደፍጠጥ ወደ አካባቢው ያለማቋረጥ ሰራዊት እያዘመተ አሰቃቂ የህዝብ ጭፍጨፋ በማድረግ ዘር ማጥፋት ፈፅሟል፡፡
ሆኖም ህወሓት የወልቃይትን ህዝብ በጥይት በመግደል ዝም ማሰኘት ሳይችል ቀርቶ ዛሬ የበለጠ ተደራጅቶበት ጠብመንጃውን ወልውሎ በአንድነት ተነስቷል፡፡ ወደ በረሃ እየወረደ አርቨኞች ግንቦት 7 እያፋፋመው የሚገኘውን አርበኝነት የሚቀላቀለውም ከዕለት ዕለት ቁጥሩ በእጅጉ አይሏል፡፡
ከሰሞኑ ደግሞ የወልቃይት ሰው ማር ዘነብ ልዩ ቦታው ቴፍ ላይ በመሰባሰብ ስለነፃነቱ መክሯል፤ የትግል መሪዎቹንም መርጧል፡፡ በጉባኤው ላይ የአርማጭሆ ህዝብም ተገኝቶ በጋራ ጠላታቸው ላይ የተባበረ ክንዳቸውን ሊያሳርፉ ቃል ተገባብተዋል፡፡
No comments:
Post a Comment