በትናንትናው ዕለት ከጎንደር ሚሊሻ ፅ/ቤት የተላኩት ደሴ እና አማረ የተሰኙት ካድሬዎች ላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ አካባቢ ሸንኮር ሜዳ-ድብሪ የተባለ ቦታ ላይ ከሰሞኑ በማውራና በሌሎች መንደሮች ውስጥ በገበሬዎችና በህወሓት ጦር መካከል ሲካሄድ የሰነበተውን ውጊያ አስመልክቶ የአካባቢውን ታጣቂዎች ሰብስበው ለማነጋገር ሲሞክሩ ታጣቂዎች እርምጃ ወስደውባቸዋል፡፡
የሸንኮር ሜዳ ታጣቂ ገበሬዎች ደሴ የተባለውን የብአዴን አሽከር የተሸከመውን ክላሽን ኮቭ ነጥቀውና ገርፈው ሲያባርሩት አማረ የተባለው ካድሬ ደግሞ ጥይት እየተተኮሰበት በገደል ተንከባሎ ለጥቂት አምልጧል፡፡
በሸንኮር ሜዳ ገበሬዎች ትጥቁን ተገፎና ተደብድቦ ተዋርዶ የተመለሰው ካድሬው ደሴ ጎንደር ከተማ ሲደርስ ደግሞ ያልጠበቀው ሁኔታ ገጥሞታል፡፡ የበላይ አለቆቹ "እንዴት መሳሪያህን አስረክበህ ትመጣለህ" በሚል አጆቹን በካቴና የፍጠኝ አሳስረው ወደ ወህኒ ሸኝተውታል፡፡
No comments:
Post a Comment