Friday, November 20, 2015

“በአማራ ብሄር ተወላጅ ወገኖቻችን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እየደረሰባቸው ያለው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ኣጥብቄ እኮንናለው” አምዶም ገብረሥላሴ -

ዜጎቻችን በስደት ሳውዲ ዓረብያ፣ የመን፣ ደቡብ ኣፍሪካ፣ ሊብያ፣ ደቡብ ሱዳንና ቤሩት የመሳሰሉ ሃገራት፤ በቀይ ባህር፣ ሜድትራንያን ባህር፣ በሲናይና ሰሃራ በረሃዎች እየደረሰባቸው ያለው መቅዘፍት ሳይበቃ በገዛ ሃገራቸው ይህን የመሰለ ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ ሊደርስባቸው ኣይገባም። ሃገራችን 15 ማልዮን በኣስከፊ ረሃብ በያዘበትና ሂወቱ እያጣበት ባለበት ግዜ ይህን መሰል ወንጀል መፈፀሙ የሚዘገንን ብቻ ሳይሆን የሚያሳፍር ወንጀል ነው። ብኣዴንም እወክለዋለውና ኣስተዳድረዋለው የሚለው ህዝብ ኣስከፊ ወንጀለ እየተፈፀመበት እያየ የሰው መሰውያ እንደለመደ ጣኦት ምንም ሳይል ደማቅ በዓል እያሳለፈ መሆኑ ያስገርማል። የኢህኣዴግ መንግስትም እንደዚህ ዓይነቶች ወንጀሎች የሚፈፅሙ ወንጀለኞች ይዞ ለፍርድ የማያቀርብ ከሆነ ኣስፍኘዋለው የሚለው ሰላም ከመደፍረሱ በላይ የወንጀሉ ተባባሪና ቁጥር ኣንድ ተጠያቂ ያደርገዋል። መንግስት ወንጀለኞች ባስቸኳይ ለህግ ያቅርብልን ! - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48377#sthash.zxUfwC16.dpuf

No comments:

Post a Comment