Saturday, November 7, 2015

መሳይ መኮንን
በረከት ቢሞትስ?!
በማህበራዊ መድረኮችና ድረ ገጾች በረከት ስምዖን ለ3ኛ ጊዜ መሞቱ እየተነገረ ነው። በግልም ሆነ በኢሳት የመረጃ ምንጮች በኩል ይህንን ዜና የሚያረጋግጥ ነገር አላገኘንም። በረከት አልሞተም። የትኩረት ማስቀየሻ ሊሆን እንደሚችል: የመረጃ መለዋወጪያ መድረኮችን የአሉባልታና የውሸት ማጠራቀሚያ በማድረግ ለማራከስ የሚደረግ ሴራ ሊሆን እንደሚችል የጠረጠሩ አልጠፉም። እኔን የገረመኝ ግን የነጻነት ፈላጊውና ታጋይ የሆነው ጎራ በእንዲህ ዓይነቱ ወሬ ጊዜውን ሲያባክን ነው። በረከት ቢሞትስ?! ከመለስ ሞት በኋላ ከህወሀት ካምፕ የትኛውም ባለስልጣን ቢሞት ምን ያስደንቃል? የኢትዮጵያ ነጻነት በስርዓቱ ሞት እንጂ ግለሰቦች በተናጠል መወገድ የሚመጣ አይደለም። ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው አጠቃላይ ስርዓቱን በማስወገዱ ላይ መሆን አለበት። በረከት ሞተ ብሎ በፌስቡክ ላይ ግርግር መፍጠር በተለይ የነጻነት ፈላጊውን ጎራ ግምት ላይ የሚጥል ነው። በሽርፍራፊ ክስተቶች ያለልክ የምንሞቅ ከሆነ ጉዞአችን አጭር: ግባችንም የማይደረስ ይሆንብናል። እናም ሙቀቱን እናብርደው። በረከት ቢሞትም ባይሞትም ለውጥ የለውም። ግን.....አልሞተም።


No comments:

Post a Comment