በጎንደር ደምቢያ ወረዳ ከየቀበሌው አራት፣ አራት ወጣቶች ተመልምለው በገበሬው ላይ ፀረ-ፕሮፖጋንዳ እንዲሰሩ ስልጠና ተሰጣቸው፡፡
በደምቢያ ወረዳ 45 የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ ሲሆን ከየቀበሌዎቹ አራት፣ አራት ወጣቶች ተመልምለው በቆላ ድባ ከተማ ጥቅምት 19 2008 ዓ.ም የአንድ ቀን ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ህዝቡ ተመልሰው ተቀላቅለዋል፡፡ የተሰጣቸው ስልጠና በዋነኝነት የሚያተኩረው በማህበራዊ ሚዲያዎች በየዕለቱ የሚሰራጩት የነፃነት ትግሉን እንቅስቃሴ የሚመለከቱ መረጃዎች ወደ ገበሬው መንደር ዘልቀው እየገቡ በመሆኑ እነሱን በማስተባበል ላይ ነው፡፡
ወጣቶቹ በተለይም ደግሞ "በኤርትራ ምንም አይነት የትጥቅ ትግል እየተካሄደ አይደለም" ብለው ለገበሬው ማህበረሰብ እንዲዋሹ የህወሓት ተላላኪ በሆነው የደምቢያ ወረዳ የብአዴን አባላት አማካኝነት በጥብቅ ተነግሯቸዋል፡፡
የህወሓት አገዛዝ ከሰሞኑ በሱዳን ድንበር አጠገብ ከበረከት ኑሪ ማዶ በሶስት ቦታዎች ላይ የልዩ ኃይል ጦሩን አስፍሯል፡፡
የልዩ ኃይል ጦር የሰፈረባቸው ሦስቱ ቦታዎች ኮረደም፣ አቡጢርና ስናር ናቸው፡፡ ህወሓት በሦስቱም ቦታዎች ያሰፈራቸው ልዩ ኃይሎች የጦር ካምፓቸውን የመሰረቱት በባለሃብቶች ይዞታ በተለይም በመጠለያቸው ላይ በመሆኑ በባለሃብቶች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል፡፡
ህወሓት በሱዳን ድንበር አካባቢ የልዩ ኃይል ጦር ያሰፈረበት ዋና ምክንያት ከሱዳን ጋር በተቀሰቀሰው ግጭት ሳይሆን እንዳልቀረ ይገመታል፡፡
በህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ማዕከላዊ ዕዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ያለምንፍ ፋታ በመክዳት ላይ ነው፡፡
የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት አባላት በስርዓቱ የሚደርስባቸው ጭቆና ከጊዜ ወደ ጊዜ መበርታቱና የተጀመረው የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ እየተፋፋመ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ እያገኘ መምጣቱ ለመክዳት እንደገፋፋቸው ታውቋል፡፡
ስርዓቱን የሚከዱ ወታደሮች በሁሉም ዕዞች ቁጥራቸው እያሻቀበና አገዛዙ ፈፅሞ ሊቆጣጠረው ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በተለይም ደግሞ መቀመጫውን መቀሌ አድርጎ በኤርትራ ድንበር ላይ ጦሩን ካሰፈረው ማዕከላዊ ዕዝ በየቀኑ የሚከዳው ወታደር የትየለሌ ነው፡፡ በአማካይ በየቀኑ ከአንድ ሬጅመንት ብቻ 6 ወታደሮች ይከዳሉ፡፡
በዚህ በሰራዊቱ ያለምንም ፋታ መክዳት ምክንያት የማዕከላዊ ዕዝ ወታደራዊ አዛዦች ከፍተኛ ስብሰባ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ በስብሰባው በሰራዊቱ ላይ እምነታቸው እየተሸረሸረ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡ መክዳቱን እንዴት ማስቆም እንደሚቻል ግን እስካሁን መላ አልመቱም፡፡
No comments:
Post a Comment