በ2008 ድርቅ
15ሚሊዮን የሚሆን ወገናችንን ሲያጠቃ ኢህአዴግ ሰፋ ብላ የድርጅቶቿን ልደት በ500ሚሊዮን በሚቆጠር ብር እያከበረች ነው።
ይህ ሁሉ ወገን በሚራብበትና በሚቸገርበት አገር ውስጥ ከሰሞኑ የተነገረው ዜና ደግሞ ጆሮ ጭው ያደርጋል።
“ጡረታ ለሚወጡ ስድስት ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በመቶ ሃምሳ አራት ሚሊዮን ብር (እያንዳንዳቸው ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ) መጦሪያ ቤቶች ተገንብተው እየተጠናቀቁ ነው” የሚል ዜና ተነገረ።
እነዚህ ቤቶች ለባለስልጣኖቹ በስጦታ መልክ የሚተላለፉት ሲሆኑ ሊሸጡት ወይም ሊለውጡት ይችላሉ ተብሏል።
ሃላፊው አቶ ተክለጻዲቅ ተክለአረጋይ (አቡነአረጋይ) ለሸገር ሬድዮ እንደተናገሩት አገራችን እነዚህን ቤቶች ለባለስልጣኖች መገንባቷ ከአፍሪካ አንደኛ ያደርጋታል ብለዋል። የመዋኛ ገንዳ (ስዊሚንግ ፑል) ያላቸው እነዚህ ቅንጡ ቤቶች የሚገነባላቸው ባለስልጣኖች ተለይተው መታወቃቸውን ተናግረዋል።
No comments:
Post a Comment