የቀበሌ አስተዳዳሪዎችና የማዘጋጃ ቤት ሹሞች አስረኛ ክፍል ጨርሰው ስራ ፈትተው የተቀመጡትን ወጣቶች እንዲሁም ዘጠነኛ ክፍልን በመማር ላይ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶችን ጭምር "በ5000 ብር ደመወዝ ስራ እንቀጥራችኋለን" በሚል ማማለያ አሽበልብለው በስልጠና ስም ባንድ አዳራሽ ውስጥ አጉረው በፖሊስ በማገት በመጨረሻም ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ጭነዋቸዋል፡፡
ለውትድርና በግዳጅ የታፈሱት በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ዕድሜያቸው ከ15-18 ዓመት የሚደርስ ሲሆን አብዛኞቹ የጎንደር ወገራ ወረዳ ጉንትር፣ ጭልፎ ወንዝና ሚጧ ቧግሽ የሚሰኙ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ናቸው፡፡
እንዲሁም በተጨማሪ የህወሓት አገዛዝ በአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ወጣቶች በአንድ ሰፊ ግቢ ውስጥ አሽጎ አግቷቸው ይገኛል፡፡ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከሎችም በቅርቡ ሊጭናቸው እየተዘጋጀ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
No comments:
Post a Comment