አይ ኤስ በኢትዮጵውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ድርጊት ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤ እና መሳይ ደጉሰው ለህዳር 8/2008 ዓ.ም ተቀጥሮባቸዋል፡፡
ፖሊስ ተከሳሾቹ ላይ የቪዲዮ ማስረጃ አለኝ በማለቱ ተከሳሾቹም ‹‹የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም በመከላከያ ማስረጃነት ስለሚያገለግለን ይቅረብልን›› ባሉት መሰረት ቪዲዮውን አይቶ ብይን ለመስጠት ለወራት ሲቀጠርባቸው ቆይቷል፡፡ በዛሬው ችሎትም ፍርድ ቤቱ መረጃውን እንዳልመረመረው በመግለፅ ለህዳር 8/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ከመሳይ ደጉሰው ውጭ ያሉት ተከሳሾች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ ተከሳሾቹ ከታሰሩ ከ6 ወር በላይ የሆናቸው ሲሆን በፍርድ ሂደቱ ከፍተኛ መጉላላት እየደረሰባቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡
No comments:
Post a Comment