መብርሓቱ ገብረእግዚአብሔር ወይም በረከት ስምኦን በበርሃ ስሙ (አንበርብር) እየተባለ የሚታወቀው ጎንደር የተወለደው ኤርትራዊ የአማራ ሕዝብ ጠላት ከኢህአፓ እስከ ብአዴን የፈፀማቸው ፀረ-ሕዝብ ተግባሮቹ ።
ይህን ሰው በሚመለከት ከዚህ ቀደም ትውልዱና የዘር ሀረጉን የቤተሰቡን ሁኔታ መጻፌና ጹሁፉ ለአንባቢያን መቅረቡን አስታውሳለሁ። ሌሎች ለሕዝብ ይፋ ያልተደረጉ ኅልቆ መስፈርያ የሌላቸውን ጉዳዮች ጊዜ ወስዶ ለማጋለጥ ይህ ባካናም ዘመን እድል ሊሰጠኝ አልቻለም እንጅ በውስጥ ከመቃጠል አላረፍኩም። ያም ሆነ ይህ በዚህ በያዝነው ወር 35ኛውን ዓመት የአማራውን ሕዝብ የገደሉበትን፤እስር ቤት ያጎሩበትን፤አካሉን ያጎደሉበትን፤ንብረቱን የዘረፉበትን፤አገር ጥሎ እንዲሰደድ ያደረጉበትን፤የዘር ፍሬውን ያመከኑበትን፤ጦርነት ውስጥ ማግደው ያስፈጁበትን፤እንደከብት ቆዳውን ገፈው በሕይወቱ ገደል የጨመሩበትን፤እቤት ውስጥ አስገብተው በሳት ያቃጠሉበትን፤ደሙን የመጠጡበትን፤የሰውነት ክፍሉን አውጥተው የሸጡበትን፤ተወልዶ ካደገበት ቀየው አፈናቅለው መሬቱን የሸጡበትን ልደት ለማክበር የቀረህን አራግፈህ ወዲህ በል እያሉ አማራውን እያመሱ ያሉበት ወቅት ላይ ስለምንገኝ እንደ አንድ የአማራ ነገድ ተወላጅ በአለሁበት ሆኜም አንደበቱ የታፈነውን አማራ ሕዝብ ድምጽ ማሰማት ኃላፊነትና ግዴታየ በመሆኑ ለዛሬ ይህን መጣጥፌን አቀርባለሁ።
በረከት ከላይ እንደተገለጸው ትውልዱ በእናት በአባቱ ኤርትራዊ መሆኑ ግልጽ ነው ተወልዶ ያደገው ጎንደር ሲሆን በረከት ያችን የጎንደሬነት ካርድ እየመዘዘ የጎንደርን ተወላጆች ከሌላው ነጥሎ ለማስመታት የሄደባቸው መንገዶች በጣም አደገኛ እንደነበሩና አሁንም ስልታቸውን እየቀያየረ እየተጠቀመባቸው እንደሆነ በግልጽ ሊታወቅበት ይገባል።ይህን ጉዳይ ነባር የኢህዴን ታጋዮችም ሆነ የአሁኖቹ የብአዴን ታጋዮች ያውቁታል።አዲሱ ለገሰ የአማራ ክልል ገዥ በነበረበት ወቅት በረከት በቀጥታ ወደ ጎንደር እየሄደ ጎንደርን አትንኩ አይነት ቃላትን እየተጠቀመ ጎንደሬ የሆኑ ካድሬዎችን ይቀጣ ነበር።ካድሬዎችን ለምን ቀጣ ሳይሆን ወደ ጎንደር መመላለስ ሲያበዛ አንድ የፈለገው ነገር እንዳለ አውቅ ነበር። 1ኛው ጉዳይ አንዳንድ አስተሳሰበ ደካማ የሆኑ ቅማንቶችን አስተባብሮ በአማራው ላይ አመጽ እንዲያነሱ ለማድረግ መሆኑ ግልጽ ነበር ይህም አሁን እየተደረገ ያለ ጉዳይ ነው። 2ኛው ጉዳይ የህወሃትን ወደ ጎንደር መስፋፋት ለማጠናከር እንደሆነም ይታወቃል። ጎንደሬ ነኝ እያለ ግን የጎንደር ሕዝብ ሥራ የማይወድና ሰነፍ ሕዝብ ስለሆነ መሬቱ ጦሙን ከሚያድር ቢለማ ምን አለበት? የምትለዋን ቃላት በስፋት ይጠቀማል።ስለጎንደር ሲነሳ ትግሬዎችም ሆኑ ትግርኛ ተናጋሪዎች አስቀድመው የሚወረውሯት ቃል ይህችው ናት።በረከት እንደ የብአዴን አመራር ከብአዴን ማ/ኮ ጋር ሳይሆን የሚማከረውና ትእዛዝ የሚቀበለው መለስ በነበረበት ወቅት ከመለስ ሲሆን አሁን ደግሞ የመለስ ራእይ አራማጅ ከሆኑ የህወሃት መሪዎች ጋር ነው። ይህን የብአዴን ማ/ኮ ሳያውቀው በስሎ የሚቀርብን ሃሳብ በተግባር ለማዋል በተናጠል እያሳመኑ እጅ እንዲሰጡ በማድረግ መሄድ የተለመደ ነበር።ዋናው ግብ በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ጎሳዎችን ውስጥ ለውስጥ በማደራጀት በአማራው ላይ አምጸው እንዲቆሙ ማድረግና በተለመደው የአማራ ጥላቻ ከአናሳዎቹ ጎን በመሆን አማራውን ለመምታት የሚጠቀሙበት መሣርያ ነበር አሁንም በዚሁ መንገድ እንደሚሄዱ ሥራዎቹ ወይም የሚፈጽሟቸው ተግባሮች በግልጽ ያሳያሉ።
የዚህን መሰሪ ሰው ተንኮል ለመመልከት ወደ ኋላ ሄጀ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፦በደርግ አገዛዝ ወቅት ህወሃት ጎንደርን በተለይም የሰሜኑን ክፍል ይዞ ነበር በ1977 ዓ/ም የተወሰነውን ቦታ ለኢህዴን አስረክቦ ሲንቀሳቀስ በመጀመርያዎቹ አካባቢ ህዝቡ ከደርግ ጋር በነበረው ጥላቻ ብቻ ተቀብሎ ማስተናገዱ አልቀረም ይህ በዚህ እንዳለ በ1978 እና በ1979 ዓ/ም ኢህዴን በሁለት ተከፍሎ የመበተን አደጋ ላይ ወድቆ ነበር።ምክንያቱ ያሬድ ጥበቡ ወይም ጌታቸው ጀቤሳ እየተባለ የሚጠራው የኢህዴን ሊቀመንበር የነበረ በኋላ ታምራትና መለስ በፈጠሩት ሴራ ጌታቸው በውጭ ሄዶ የማደራጀትና ኢህዴንን የማጠናከር ሥራ እንዲሰራ ተብሎ ወደ ውጭ ወጣ የሱን ቦታ ታምራት ተካ።በዚህ ወቅት አብዛኛው ታጋይ በታምራት ላይ ቅሬታ ያሳደረና በጌታቸው መነሳት ቅሬታ የተሰማው ነበር። ጌታቸው ሳያኮርፍና ተስፋ ሳይቆርጥ ኢህዴንን የማጠናከር ተግባሩን ቀጥሎ ተጓዘ በየጊዜው የሚፈጽመውን ተግባርም አገር ቤት ላለው የኢህዴን ማ/ኮ ሪፖርት ያደርግ ነበር።መልእክቱ ከአሜሪካ ወደ ሱዳን በህወሃት መስመር ይላካል የራዲዮ መልእክት የጹሑፍ ይላካሉ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የህወሃትን በጎ ፈቃድ ማግኘት ነበረበት።ከእለታት አንድ ቀን ህወሃት የኢህዴንን የጹሑፍ መልእክት ይጠልፍና ፖስታው ተከፍቶ ይነበባል የሰው ስም ዝርዝር ያለበት ነበር ጌታቸው የላከው ለኢህዴን አባልነት፤ደጋፊና ተባባሪ ይሆናሉ የተባሉትን ስም የያዘ ደብዳቤ።
ኋላስ ምን ሆነ? አጅሬ ህወሃት ይህን ደብዳቤ አፍኖ ከቆየ በኋላ በውጭ ያለውና በአገር ቤት ያለውን የኢህዴን አመራር በጥርጣሬ ላይ አክርመው ደብዳቤው እጃቸው መግባቱንና ጌታቸው የመለመላቸው ሰዎች ለኢህዴን አደገኛ ስለሚሆኑ ኢህዴንን ከአደጋ ለመከላከል ስንል ያደረግነው ነው ተብሎ በበጎነት እንዲታይና የኢህዴን አመራር እምነት እንዲጥሉበት ተደረገ።አደጋው ግን ለኢህዴን ሳይሆን ለህወሃት እንደነበር ግልጽ ነበር ይህ ይፋ ሲሆን የኢህዴን አባላትና አመራር በጌታቸውና ታምራት ቲፎዞነት ሲጦዝ ከረመ ህወሃትና ኢህዴን በጹሑፍ መባጠስ የጀመሩበት ወቅትም ነበር ዋናው ነጥብ አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘርዓ ጽዮንን በገዳሪፍና ካርቱም የኢህዴን ጽ/ቤት በማስተናገዱ ህወሃትን ደፍሯል የሚል ሲሆን ኢህዴን ደግሞ ምሥጢሬን አይታችኋል በሚለው ዙርያ ነበር።በዚህ ወቅት አያ በረከት ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሲሸመገል የነበረው ከጌታቸው ወገን በመሆን ሲሆን እስከ መቼ የህወሃት ሸሚዝ ሆነን ልንኖር ነው በማለት አኩራፊ ነበር ይህች ግን በነመለስ ቅንብር ከጌታቸው ጎን ገፍተው የሚወጡትን የአማራ ተወላጆች ለማጥመድና ጊዜ ገዝቶ(ጠብቆ)ፀጥ ለማድረግ ያለመ ነበር ተሳካ። የበረከት ወንድም ካሣሁን የተገደለው በህወሃትና በኢህአፓ በተደረገ ጦርነት ከህወሃት በተተኮሰ ጥይት ነው ይህ ግን ለበረከት ምኑም አልነበረም በሬ ካራጁ ብንልም የበረከት ዓላማ ሌላ ነበርና ዛሬ ላይ ሆነን በረከት የመጣበትን መንገድ ስንመለከት ዘለቀ፤ሙሉዓለም፤ጌጡ(ኡስማን)፤አውጃኖ፤አገኘሁ፤ንጉሤ...ወዘተ የተገደሉበትን ሁኔታ በገሃድ ያስያል።
ሌላው በረከት በአማራ ህዝብ ደም ምን ያህል እንደቀለደ የሚያሳየው በ1984 ዓ/ም ደቡብ አካባቢ ምክንያቱ ኦነግን ያደረገ ነገር ግን ኢህአዴግ በዋናነት የመራው በሐረር፤በአርባ ጉጉ፤ወተርና እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የአማራ ነገድ ባላቸው ምስኪን ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመው እልቂትን አስመልክቶ እኔ ከደሙ ንጹሕ ነኝ በማለት ማስረጃዎች ተቀብረው የሚቀሩ ይመስል ነገርን ከራስ አውርዶ ለመጣል በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አማራዎችን ሆድ ለማባበል ሲባል የጎንደር 21 ቀበሌዎች ያዘጋጁት እንዲባልና ኢህዴን ወደ ብአዴንነት ሽግግርን በሚያደርግበት ወቅት ለደቡብ አማራዎች ትርንስፖርት ተዘጋጅቶ ጎንደር ከተማ ድረስ እንዲሄዱ ተደርጎ ሰፊ ድግስ ተደርጎ የደቡብ አማራ ወገኖቼ አይዟችሁን ተችረው እንዲመለሱ የተደረገው ትራጀዲ ወደ ኋላ ተመልሸ ሳስበው ያመኛል።በድርጅት ገንዘብ ወጭ ተመድቦ ነገር ግን ገንዘቡ ደብዛው ጠፍቶ ዝግጅቱ በ21ዱ ቀበሌዎች በጀት ተሸፈነ። ያ ዝግጅት በጎንደር አማራዎችና ከደቡብ ወገኖቹ በመጡ አማራዎች መካከል ልብ ለልብ ያገናኘ ከበረት የጠነከረ አንድነትን ፈጥሮ ነበር የሚያሳዝነው ነገር ያኔ የተወረወረች የውሸት አይዟችሁ ለምን ከክልሌ መጣችሁብኝ በማለት በሽፈራው ሽጉጤ ፊታውራሪነት በጉራ ፈርዳና በቬንሻንጉል በጋምቤላ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች አማራን አያሳየኝ በማለት ምስኪን ወገኖቻችን ሲያልቁ የደረሰላቸው አልተገኘም በራሳቸው የአማራ ክልል በሚባለው እንኳን የሚተባበራቸው ጠፍቶ የአማራው ገዥዎች ጀርባቸውን ሲሰጡ ተመልክተናል።
ዛሬ የ35ኛ ዓመታችን ልደት ልናከብር ስለሆነ ገንዘብህን አምጣ የሚሉት ደሙን መጥምጠው የጠቡትን አጥንቱን የጋጡትን አማራ ምን አለውና ነው ገንዘብ የሚጠየቀው? ለነ ህላዊ ታደሰና ዓለምነው መኮንን ፈንጠዝያ ወይስ የአማራው ህዝብ እንባ አባሽና ድምጽ ለሆነ ድርጅት? መንደር ለመንደር የእያንዳንዱን አርሶ አደርና አባወራ ቤት በማሰስ አስገድዶ ገንዘብ መሰብሰብ ሊቆም ይገባዋል። ማን አለብኝነት ለደርግ አልበጀም ይህ ሕዝብ ሆ!! ብሎ ሲነሳ የሚከፈለው ዋጋ እጥፍ ድርብ እንደሚሆን መዘንጋት አይገባም ዛሬ ሆድህን ወደህ አንድነትን ከሚንዱ የውጭ ጌቶቻቸውን ለማስደሰት ታሪክ ከሚያጠፉ፤አገር ከሚሸጡ የሀገር ሀብት ከሚዘርፉና ትውልድን እየበሉ ከሚገኙ ፀረ-ሕዝቦች ወግነህ ዜጐችህን እያጫረስክ ያለህ ካድሬ፤የደህንነትና የፖሊስ ኃይል፤የመከላከያ ሰራዊት የአማራውን ሕዝብ ክንድ ጠምዝዘህ እያሳረድክ ያለህን እያንዳንድህን ታሪክ ስለሚፋረድህ ነገ ይህ የአማራ ነገድ ሕዝብ አንገቱን ቀና አድርጎ መሄድ ሲጀምር መሬት ከምትጠብህ አሁን ታሪክ ለመስራትና ከወገንህ ጐን ቆመህ አይዞሽ እማየ!! አይዞህ አባየ!! አይዞህ ወንድም ዓለም!! ይዞሽ እህት ዓለም!!ማለት ብትሞክር ትናንት ለግል ጥቅም ስትል የፈጸምክበትን በደል ሁሉ ይቅር ሊልህ እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ።
የአማራ ህዝብ አማራ ባልሆኑ መሪዎች አይገዛም!http://ecadforum.com/Amharic/archives/15802/
No comments:
Post a Comment