Saturday, November 7, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ አምስት ቀበሌዎች በድርቅ መጠቃታቸው ታወቀ፡፡ ====================================================


በከፍተኛ ድርቅ ተመትተው ነዋሪዎቻቸው ክፉኛ ለጠኔ ተጋልጠው የሚልሱት የሚቀምሱት በማጣታቸው ከሞት አፋፍ ላይ ሆነው የሚገኙባቸው አምስቱ ቀበሌዎች ጨጨሆ፣ ፈንጠርያ፣ ቀንጠብጣ፣ አይጠላ እና እንድ ሌላ ለጊዜው ስሙን ያላወቅነው ቀበሌ ናቸው፡፡

በሰሜን ጎንደር የወገራ ወረዳዎቹን ሶሚያ፣ ጓሪ፣ ግጭሆ እና ቧግሽ የተባሉትን አራት ቀበሌዎች ጨምሮ እስካሁን ዘጠኝ ቀበሌዎች ክፉኛ በድርቅ ተመትተው ከ50ሺህ እስከ 60 ሺህ ህዝብ ተርቦ የስደትና ዕልቂት ደመና እያንዣበበበት ይገኛል፡፡
አገዛዙ ለፖለቲካ ወሬ ፍጆታው ለስሙ እንዲ አደረግሁ ለማለት ብቻ 10ሺህ ኩንታል በቆሎ ችፋንዝ ላይ ያራገፈ ሲሆን ከ9-10 ቤተሰብ ለሆነ ከ10-15 ኪሎ ግራም በቆሎ ብቻ እየታደለ ይገኛል፡፡ ይህም ለአንድ ቀን ምሳ እንኳን የሚበቃ እንዳልሆነ የረሃቡ ሰለባዎች ብሶታቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡
እንዲሁም ለእርዳታ ችፋንዝ ላይ የተራገፈው በቆሎ በአንድ መጋዘን ውስጥ አንድ ላይ መከማቸት ሲገባው በየግለሰቦች መኖሪያ ቤት በመከፋፈል ተከማችቶ ለወዛደርና ለቤት ኪራይ በሚል ሰበብ እየተቀነሰ በሰፊው እየባከነ ይገኛል፡፡
ለእርዳታ በልመና የተሰበሰበን ገንዘብ ለጦርነት ማዋል፣ የካናዳ ስንዴ መሸጥ፣ የእርዳታ እህል በሚከፋፈልበት ጊዜ የከረጢቱን ዋጋ በማስከፈል በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መሰብሰብ እና ከውጭ የመጣን እርዳታ ስርዓቱን የሚደግፉትን ብቻ እየለዩ መለገስ በህወሓት ቤት የተለመደ እና ካድሬዎቹ በህዝብ ዕልቂት ላይ ክፉ ቀን ጠብቀው የሚቆምሩት የህይወት ቁማር ነው፡፡ 
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)

No comments:

Post a Comment