Thursday, November 26, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


በጎንደር ላይ አርማጭሆ በህወሓት አገዛዝ ጦር ኃይልና በገበሬዎች መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ሰላማዊ ዜጎች በስውር በመገደል ላይ ናቸው፡፡
በጎንደር ላይ አርማጭሆ ማውራ መንደር ላይ ተጀምሮ ወደ ሌሎች ቀዬዎች የተስፋፋው ወህሓትን በጦር መሳሪያ የማስወገድ እርምጃና በአካባቢው የነገሰው ከፍተኛ ውጥረት አሁንም ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን የህወሓት የታጠቁ ቡድኖች ጠብመንጃ አንስተው ዱር ያልወጡ ሰዎችን ጨለማን ተገን እያደረጉ ተኩሰው በመግደል ሰላማዊ ወገኞቻችንን የጥቃታቸው ዋነኛ ኢላማ አድርገዋቸዋል፡፡
ሰሞኑን በጨለማ በጥይት ተደብድበው በግፍ ከተገደሉት በርካታ ወጣቶች መካከል የሮቢት ነዋሪ የሆነው አበበ እንየው የተባለው ይገኝበታል፡፡ ወጣቱ አበበ እንየው ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ለይ ነው የህወሓት ገዳይ ቡድን ጥይት ሰለባ ለመሆን የበቃው፡፡
በአሁኑ ጊዜ በጎንደር ላይ አርማጭሆ እንዲሁም በጭልጋ ጭምር ትምህርት ቤቶችና ሁሉም የአገዛዙ መስሪያ ቤቶች ተዘግተው የስራ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ቆሟል፡፡ በመሆኑም በላይ አርማጭሆና በጭልጋ ከጦር ኃይሉ በስተቀር የህወሓት አገዛዝ የፖለቲካ መዋቅር አለ ለማለት አስቸጋሪ እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
በተያያዘ ዜናም በጎንደር ደምቢያ ወረዳ የሚሊሻ ጉጅሌ ኮማንደር በሆነው አራጌ የተባለ የህወሓት-ብአዴን አገልጋይ ላይ የመግደል ሙከራ ተደርጎ አካባቢው መጠነኛ ውጊያ እንዳስተናገደ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ዜና ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment