በርሃብ ለተጠቁት ኢትዮጵያውያን ለሁለት ቀን የሚቆይ የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻ ሊደረግ ነው፡፡ ዘመቻው አርብ ህዳር 3/2008፣ እና ቅዳሜ ህዳር 4/2008 እንደሚደረግም ታውቋል፡፡ ዘመቻውም በእንግሊዘኛ #EthiopiaFamine እንዲሁም በአማርኛ #ክፉ_ቀን በሚል መለያ (ሀሽ ታግ) ይደረጋል፡፡
በመጀመሪያው ቀን ስለ ርሃቡ መረጃዎች በመለዋወጥ፣ ለኢትዮጵያውያን፣ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰቡና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ርሃቡን በማሳወቅ እንዲሁም የሁለተኛው ቀን ዘመቻ መፍትሄዎችን በማፈላለግ በተለይም በርሃቡ የተጠቁትን በምን መልኩ መርዳት እንደሚቻል በመወያየት ላይ እንደሚያተኩር ተገልፆአል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ርሃቡ በተከሰተባቸው አካባቢዎችና የርሃቡ ተጠቂዎች የተሰደዱባቸው ከተሞችና አካባቢዎች የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ያጋጠማችሁን፣ ያላችሁን መረጃ በተለይ በፎቶና በቪዲዮ አስደግፋችሁ በነገረ ኢትዮጵያ የፌስ ቡክ ገፅ ብትልኩልን፣ እኛም ለህዝብ እንደምናደርስ እንገልፃለን፡፡ በተጨማሪም በርሃቡ ላይ የግል ትንታኔዎች፣ የመፍትሄ ሀሳቦች ያላችሁ በነገረ ኢትዮጵያ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
No comments:
Post a Comment