Sunday, November 22, 2015

በገዢው የኢህአዴግ

ስርአት በሃገር መከላክያ ሰራዊት የሚገኙ ቲሞችና ጋንታዎችን በአሁኑ ሰአት የሰው የሃይል ብዛታቸው እተዳከሙ እንደሚገኙ በመከላክያ ሰራዊት ውስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን የላኩት መረጃ ገለፁ።
በመረጃው መሰረት በገዢው የኢህአዴግ ስርኣት በአገር መከላክያ ሰራዊት የሚገኙ ቲሞችና ገንታዎች በአሁን ሰኣት በተለያዩ ምክንያቶች የሰው ሃይል ብዛታቸው እየተዳከሙ እንደሚገኙ ከገለፁ በኃላ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በሰው ሃይላቸው የተዳከሙ ክፍሎች ለሞምላት በሚል ምክንያት ከ 4ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎች ወደ ውትድርና ለመግባት ማስጣወቂያ ቢያዘጋጅም ይሁን እንጂ ባሰቦው መንገድ ሊከናወን አለመቻሉ የተነሳ በተወሰኑ ክልሎች የሚገኙ ወጣቶች ግን አስገድዶ ወደ ውትድርና ለማስገባት መምርያ አውርዶ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው በመጨረሻ የመከላከያ ሰራዊት በአሁን ግዜ በሰው ሃይል በመዳከሙ ምክንያት አዲሶች ወጣቶች መጀመርያ በምዝገባ ሂደቱ የሚነገራቸው ቃል ከነባሩ ሰራዊት ጋር ከትቀላቀሉ በኃላ የተነገራቸው ቃል ስለ ማይተግበር፤ በሰራዊት ላይ የሚፈፀም ግፍና በደል እንዲሁም በጥቅማ ጥቅም አድልዎ ስለሚበዛ ያገኘነው ፋይዳ የለም በማለት ከሰራዊቱ ሸሽተው ለመሄድ እንደሚገደዱ መረጃው አክሎ አስረድቷ።


No comments:

Post a Comment