Tuesday, November 17, 2015

በእንቅርት ላይ ጀሮ ደገፍ 
።።።።።።።።።።።።

በማይጨው ከተማ ከ105 በላይ ቤቶች ለከተማ ውበት በሚል ሰበብ እየፈረሱ ነው።
በማህበር ተደራጅተው፣ በራሳቸው ቤት የሰሯቸውና የብረታብረት፣ የእንጨት ስራ፣ ጋራዥ፣ ቁርስና ሻሂ፣ የተለያዩ ሸቀጦች የሚሰራባቸው ቤቶች በሃይል እየፈረሱ ነው።

በነዚህ ቤቶች ሲሰሩ የነበሩ ወጣቶችና ቤተሰቦች ያለ ካሳ፣ ያለ ቅያሪ መስርያ ቦታ እንዲያፈርሱ እየተገደዱ ነው።
ቤታቸው የፈረሰባቸው ወጣቶች ስራ ኣጥተው ለስደት እንዲሄዱ እየገፋፏቸው ይገኛሉ። ቆየት ብሎም የሚሰደዱ ወጣቶች በኣቋራጭ ለመበልፀግ የሚል ቅጥያ ይሰጣቸዋል።
በእንቅርት ላይ ጀሮ ደገፍ እንደሚባለው ህዝቡ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ እየተሰቃየና እየሞተ ባለበት ሰዓት ቤቱ ፈርሶ በረሃ ላይ እየጣሉት ነው።
በሌላ ዜና 
።።።።።።

በራያ ዓዘቦ ወረዳ ሓደ ኣልጋ ቀበሌ ኑዋሪ የሆኑት የዓረና ኣባላት " ለናንተ የሚሆን እርዳታየለንም ዓረና ይስጣቹ " በሚል ምክንያት የእርዳታ እህል ከሚታደልበት ጨርጨር ተባረዋል።
ሑመራ
።።።።

በቃፍታ ሑመራ ኣደባይ ቀበሌ ሕለት ኳኳ ትምህርት ቤት 80 ተማሪዎች በድርቅ ምክንያት ትምህርታቸው ኣቋረጡ። ሕለት ኳኳ የኩናማ ብሄረሰብ በብዛት የሚንርባት ስፍራ ነች።
በምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሑመራ ወረዳ ድርቅ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ህዝቡ ኣስቸኳይ እርዳታ እየጠየቀ ነው።
EthiopiaFamine

ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO.

No comments:

Post a Comment