(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
በላይ አርማጭሆ ሙሴ ባንብ የሚገኙ 10 የእህል ወፍጮዎች በኤሌክቲሪክ ኃይል እጥረት ሙሉ በሙሉ በመቆማቸው ባለቤቶች ለከፍተኛ ኪሳራ ህዝቡ ደግሞ ለከፋ ችግር ተጋልጧል፡፡
የወፍጮዎቹ ባለቤቶች እስከ "ክልል አስተዳደር" ድረስ የተከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ተቀርፎ ሰርተው መብላት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ደጋግመው አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ከረጅም ጊዜ መጉላላት በኋላ ለትራንስፎርመር መግዣ 1 ሚሊዮን ብር አዋጥተው እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል፡፡
የወፍጮዎቹ ባለቤቶች በአሁኑ ወቅት ተስፋ ቆርተው ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ የሙሴ ባንብ ነዋሪዎች ደግሞ ለህወሓት ባላቸው የመረረ ጥላቻ ምክንያት እየተፈፀመባቸው የሚገኝ በቀል መሆኑን በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment