Saturday, November 14, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


ከፍተኛ ቁር ያለውን የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ጭኖ ከጎንደር ወደ ትክል ድንጋይ አቅጣጫ ሲያመራ ከርከር ባለእግዚአብሄር አካባቢ ሲደርስ ገደል የገባው የጦር ተሽከርካሪ ከገበሬዎች በተሰነዘረ ጥቃት እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ በአደጋው የሞቱ ወታደሮች በሙሉ ትጥቃቸው ተዘርፏል፡፡
ልዩ ስልጠና ሲሰጣቸው ቆይተው ወደ ዳንሻና አብደራፊ ሲያመሩ የነበሩትን በርካታ የ24ኛ ክፍለ ጦር አባላት ጥስቅ አድርጎ እንደጫነ ጅው ወዳለ ገደል ተወርውሮ በመግባት እንደሸክላ እንክትክት ያለው ዑራል መኪና አደጋው በደረሰበት ከርከር ባለእግዚአብሄር አካባቢ አድፍጠው በነበሩ የገበሬ ሸማቂዎች ጥይት ጎማው ሳይመታ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው፡፡
በመኪና ላይ ተሳፍሮ የነበረ ወታደር ለወሬ ነጋሪ እንኳን አንድም እንዳልተረፈ ተረጋግጧል፡፡ የሟቾች ቁጥር በትንሹ ከ100 በላይ እንደሆነ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምንጮቻችን በአስከሬን ምርመራ ክፍሉ አካባቢ ያደረጉትን የጥድፊያ ቆጠራ መሰረት በማድረግ ገልፀውልናል፡፡
ዑራሉ ገደል በገባበት ቅፅበት ከየት መጡ ያልተባሉ ሰዎች ድንገት ከተፍ ብለው በአደጋው ያለቁ ወታደሮችን ትጥቅ በሙሉ ጠራርገው ይዘው ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)

No comments:

Post a Comment