በላዕላይ አድያቦ
ወረዳ የሚኖር ህዝብ ለገዢው የሕወሓት/ኢህአዴግ አስተዳደሮች በሚደረጉ ስብሰባዎች ከናንተ የምንጠብቀው መልካም ነገር የለም በማለት ላይ እንደሚገኝ ታወቀ።
በመረጃው መሰረት በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ ወረዳ የሚኖር መላው ህብረተሰብ አስተዳደሮችና ካድሬዎች ስብሰባ እያሉ በመጥራት መንግስት ያቀዳቸው የእድገት መንገድ ስላለው መንግስታችን የሚለንን መተግበር አለብን እያሉዋቸው ባሉበት ጊዜ ህዝብ በበኩሉም ከናንተ የምንጠብቀው እድገት ይሁን ልማት የለም። የናንተ ለውጥ በቃላት እያደናገራቹ በድህነት መኖር ነው ይህንን መሆኑን አውቀን ባለፈው ምርጫ ለናንተ አልመረጥንም ማን መረጣችሁ እየመራችሁን ያላቹ በማለት እየተቃወማቸው ስላለ ለአንዳንድ አነሳሾች በማለት እያስፈራሩዋቸውና እያሰርዋቸው እንደሚገኙ ተገለፀ።
የወረዳው ነዋሪ ህዝብ በሕወሓት/ኢህአዴግ መልካም አስተዳደር ብሉሽነት ምክንያት እጅግ ስለ ተማረረ በአስተዳደሮቹ ለማስመሰል ተብሎ የቀረበውን እድገትና ልማት በሚል የመቀስቀሻ ቃላት በመንፈግ በተቃራኒው ልጆቻችን በናንተ ሰበብ ስራ አጥተው በሰህራና በባህር እየጠፉ በመሞት ላይ ናቸው፤ እናንተ የወቅቱ የዝናብ እጥረት እንዳጋጠመ እያወቃችሁ ለተቸገረው ህዝብ የሚሆን የእርዳታ መንገድ ለምን አታመቻቹለቱም፤ መናገር ብቻ ምን ያደርግልናል፤ ለ24 አመታት ያህል ተሸክመናችዋል ከእንግዲህ ወዲያ ግን ከላያችን ላይ ብትወርዱ ይሻላል በማለት በጥያቄ ወጥረው እንደያዟዋቸው ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል።
No comments:
Post a Comment