Monday, August 14, 2017

ኑ! እና ፈቃደ ሸዋቀናን እንዘክር

እንደ አውሮፓ አቆጣጠር እሁድ ኦገስት 27,2017 ታጋዩን ምሁር አቶ ፈቃደ ሸዋቀና የሚዘክር መታሰቢያ ተዘጋጅቷል። በእለቱ የአንጋፋው ምሁር ፈቃደ ሸዋቀና የህይወት ጉዞና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያደረገው አስተዋጽኦ በሰፊው ይገለጻል። ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ፣ የትግል አጋሮቹና የተለያዩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። ከዚህ በተጨማሪ በፍቃደ ሸዋቀና ስራዎች ዙሪያ የተዘጋጁ ዘጋቢ ፊልምና መጽሔት ለህዝብ ይፋ ይሆናል።
ቦታ፥- US Naval Memorial
701 Pennsylvania Avenue, NW Washington DC 2004
የዝግጅቱ ሰአት ከ 3:00pm እስከ 7:00pm

ማስታወሻ፥
ቦታው ለሜትሮ ባቡር (Archives/Navy Memorial) ለመጠቀም አመቺ ሲሆን አዘጋጅ ኮሚቴው ከ PMI ፓርኪንግ ጋራዥ ጋር በመነጋገር በ875 D street, NW ላይ የሚገኘው የፓርኪንግ ስፍራ ቅናሽ ማግኘቱን ያስታውቃል።
እሁድ August 27, 2017 
ኑ! እና ፈቃደ ሸዋቀናን እንዘክር።
ለበለጠ መረጃ በ 571-275-7005 ወይም 571-970-8432 ይደውሉ።
አዘጋጅ ኮሚቴው

Image may contain: 1 person

አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ አምስት አምባሳደሮች ወደ ሀገር ቤት ተጠሩ (ኢሳት ዜና–ነሐሴ 8/2009)

አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ አምስት አምባሳደሮች ወደ ሀገር ቤት መጠራታቸው ተዘገበ።Bilderesultat for አምባሳደር ግርማ ብሩ

በተጠሩት አምባሳደሮች ምትክ አዳዲስ ግለሰቦች እንደሚሾሙም ተመልክቷል።
በማይታወቅ የገንዘብ ምንጭ በተለያዩ የንግድ ተቋማት ውስጥ ባለድርሻ መሆናቸው የሚገለጸው አምባሳደር ግርማ ብሩ የጸረ መስናው ዘመቻ እስኪያቆም በሕክምና አሳበው ሊዘገዩ እንደሚችሉም የቅርብ ምንጮች ይገልጻሉ።
በዩ ኤስ አሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ከአቶ ግርማ ብሩ በተጨማሪ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ስዩም መስፍን በተመሳሳይ ወደ አዲስ አበባ ተጠርተዋል።

በእንግሊዝ ለንደን በተካሄደው 16ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የ7ኝነት ደረጃን አገኘች። (ኢሳት ዜና–ነሐሴ 8/2009)

ከአፍሪካ ደግሞ የ3ኝነት ደረጃን ይዛለች። ኢትዮጵያ እነዚህን ደረጃዎች የያዛቸው ሁለት የወርቅና ሶስት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ነው። ቅዳሜ ምሽት በተካሄደው የወንዶች 5ሺ ሜትር ውድድር አትሌት ሙክታር እድሪስ ሞፋራህን በማሸነፍ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሩ ማስገኘቱ ታውቋል። በ5ሺ ሜትር ሴቶች በ10 ሺ ሜትር ርቀት ወርቅ ያስገኘችው አልማዝ አያና ሁለተኛ በመውጣትና የብር ሜዳሊያ በማግኘት ለሀገሯ ሁለት ሜዳሊያዎችን አበርክታለች። ጥሩነሽ ዲባባ ደግሞ በ10 ሺ ሜትር 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ማስገኘቷ አይዘነጋም። በወንዶች ማራቶን አትሌት ታምራት ቶላ በውድድሩ ሁለተኛ በመውጣት ለሀገሩ በሻምፒዮናው የብር ሜዳሊያ ማስገኘቱ ይታወሳል። እሁድ ምሽት በተጠናቀቀው 16ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አሜሪካ በ10 የወርቅ፣በ11 የብርና በ9 የነሀስ ሜዳሊያዎች ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች። ኬንያ ደግሞ በድምሩ 11 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ስትሆን ደቡብ አፍሪካ በ6 ሜዳሊያዎች የ3ኝነት ደረጃን ይዛለች። ኢትዮጵያ ደግሞ ሁለት የወርቅና ሶስት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሻምፒዮናውን በ7ኝነት ደረጃ ስታጠናቅቅ ከአፍሪካ ደግሞ የ3ኝነት ደረጃን ይዛለች። በ16ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 43 ሀገራት በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባታቸውን ዘገባው አመልክቷል።Image may contain: one or more people and text

በኢህአዴግ ታሪክ ሦስተኛው እንደሆነ የተነገረለት የጸረ ሙስና ዘመቻ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አይነኬ የሚመስሉ ባለሐብቶችንና ድርጅቶችን በር ማንኳኳት የጀመረ ይመስላል፡፡


 በአገሪቱ ግዙፍና ስመጥር የመንገድና የሕንጻ ተቋራጮች ሒሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ በፍርድ ቤት እግድ መጣሉ ለዚህ እንደማስረጃ እየተጠቀሰ ነው፡፡
ከነዚህ ግዙፍ ተቋራጮች መካከል ስመጥሮቹ አሰር ኮንስትራክሽንና ገምሹ በየነ (Gemecon) ደረጃ አንድ ጠቅላላ ኮንትራክተር ይገኙበታል፡፡ የገመኮን መንገድ ተቋራጭ ድርጅቱ ባለቤት አቶ ገምሹ በየነ ከጥቂት ቀናት ጀምሮ የት እንደገቡ አልታወቀም ተብሏል፡፡ ስመጥር ባለሀብት ከአገር ሾልከው ሳይወጡ እንዳልቀረ ይጠረጥራሉ፡፡ ምክንያታቸውን ሲያስረዱም ባለፉት ሰባት ቀናት ውስጥ ቢሯቸው አለመግባታቸውን ያነሳሉ፡፡
አንድ የኢሊሌ ሆቴል የጥበቃ ባልደረባ ከሁለት ሳምንት በፊት ጸጉራቸውን በራሳቸው ሆቴል ውስጥ በሚገኝ የውበት ሳሎን ሲስተካከሉ እንደተመለከቷቸውና ከዚያ ወዲህ ግን ወደ ሆቴላቸው ዝር እንዳላሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ በስም መጠቀስ ያልፈለገ ሌላ የሆቴሉ ማኔጅመንት አባል ‹‹ለዕቃ ግዢ ከአገር መውጣታቸውን ነው የማውቀው፤ በእርግጠኝነት ይመለሳሉ›› ሲል ተናግሯል፡፤
በአገሪቱ ከሚገኙ በጣት ከሚቆጠሩ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች አንዱ የሆነውና በካዛንቺስ አካባቢ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ጀርባ የሚገኘው ኢሌሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በአቶ ገምሹ በየነ ባለቤትነት የተያዘ ግዙፍ ሆቴል ሲሆን ከአዲስ አበባ መስተዳደር በቅርብ አመታት ውስጥ ባገኘው 1690 ካሬ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በአገሪቱ ታሪክ የመጀመርያውን ባለ አምስት ፎቅ የመኪና ማቆምያ በ258 ሚሊዮን ብር ገንብቶ በከፊል ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ከዚህም ባሻገር በቡራዩና በቢሾፍቱ ግዙፍ ሪዞርቶችን ለመገንባት ላይ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በመንገድ ግንባታ በአሁኑ ወቅት ከ3 ቢሊየን ብር የማያንሱ ፕሮጀክቶች በእጁ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ በትግራይና አማራ ክልል ከማሃበሬ እስከ ዲማ፣ ከዲማ እስከ ፈየል ዉሀ፣ እንዲሁም ከአዘዞ እስከ ጎርጎራ፣ከድሬዳዋ እስከ ደዋሌ፣ በዚሁ የመንገድ ተቋራጭ የተገቡ ናቸው፡፡ ገመኮን የመንገድ ተቋራጭ እና የሆቴል ፕሮጀክቱን ጨምሮ አቶ ገምሹ በየነ በሥራቸው ከ7ሺ የማያንሱ ጊዝያዊና ቋሚ ሠራተኞችን ያስተዳድራሉ፡፡
አቶ ገምሹ በየነ የኦሮሚያ ክልል የወጣቶችን አመጽ ለማብረድ በተወጠነው የኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ከሚገኙ ባለሐብቶች መካከል አንዱ ሲሆኑ የርሳቸው ድርጅት ከሙስና ጋር በተያያዘ ስሙ መነሳቱ የጸረ ሙስና ዘመቻው ውስጥ የኦህዴድ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እጅ እንዳለበት አመላካች እንደሆነ የሚያምኑ በርካቶች ናቸው፡፡ @ዋዜማGemshu-Beyene

Sunday, August 13, 2017

የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሃት/ኢህአዴግን እንደማይፈልግ በህይወት መስዋዕትነት አረጋግጧል ስለሆነም የትግል አጀንዳችን፡ "ሕወሃት/ኢህአዴግ ይውረድ፤ የባለአደራ መንግስት ይቋቋም!!!! የሚል መሆን አለበት!!


(ከሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የተላለፈ የትግል ጥሪ)
የኢትዮጵያ ህዝብ የሀገሩና የስልጣን ባለቤት ሆኖ የሚፈልገውን ለመሾምና ያልፈለገውን ለመሻር የሚያስችል ህጋዊ ስርዓት እንዲመሰረት ባለፉት አመታት እጅግ መራራ ትግል አድርጓል፡፡ የትግሉ ደረጃም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ሂዶ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከዚህ በፊት ከተለመደው ውጭ የማንንም የተደራጀ ሀይል አመራር ሳይጠብቁ እንደ አካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን በማንገብ ከታጠቀው አገዛዝ ጋር ባዶ እጃቸውን በራሳቸው ፈቃድ ተጋፍጠዋል፡፡ በቆራጥነት በተከፈለው የህይወት መስዋዕትነት በብዙ ኢትዮጵያውያን ላይ በተፈጠረው ቁጭትና እልህ የትግሉ አድማስ እየሰፋ ሀገራዊ ቅርፅ እየያዘ መጥቷል፡፡ ትግሉ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች ከፍተኛውን የህይወት መስዋዕትነት ዋጋ ከፍለዋል፡፡Image may contain: 2 people, people standing
ሁላችንም እንደምንገነዘበው አሁን በላያችን ላይ የተጫነው አገዛዝ ለስልጣኑ ህልውና መሰረት አድርጎ የያዘው ስልት የኢትዮጵያውያን የጋራ እሴቶችን ማጥፋትና በልዩነት ላይ የተመሰረተ ጥላቻን እና አለመተማመንን መሰረት ያደረገ የከፋፍለህ ግዛው የአገዛዝ ዘይቤ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በጋራ የምንጋራቸውን ማለትም ሀይማኖትን እና ሀይማኖተኝነትን አዋርዷል፤እውቀትና አዋቂዎች ክብር እንዲያጡ አድርጓል፤ሽምግልና እና ሽማግሌዎችን በኢትዮጵያ ማህበራዊ አደረጃጀት ላይ ያላቸውን ሚና እንዲያጡ አድርጓል፤የኢትዮጵያ ልጆች ቋንቋ፣ባህል፣እምነት የመጡበት አካባቢ ሳይለያያቸው በአንድ ጉድጓድ እየተቀበሩ የገነቡትን ብሔራዊ ክብርና የሃገር ሉዓላዊነት መንፈስ አዳክሟል፤በኢትዮጵያ ውስጥ እሱ የማይቆጣጠረው የሙያና የሲቪክ ማህበር እንዲኖር ባለመፈለጉ ሀገሪቱን በሁሉም ዘርፍ ምድረ በዳ እና የተቋም ደሃ አድርጓታል፡፡ 
ይህም አሁን ያለው አገዛዝ የሚከተለው የአገዛዝ ዘይቤ ጣሊያን ሀገራችንን ቅኝ ለመግዛት በሞከረበት አ

( የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ) የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ መዓዛው ጌጡ ይናገራሉ ፡፡


አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ እስከ አሁን ድረስ ስላደረጋቸው እንቅስቃሴዎች እና ወደፊት ስለወጠናቸው እቅዶች ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ አብራርተዋል፡፡ 
አርበኛ ታጋይ መዓዛው ጌጡ በሰጡት የሬድዮ ማብራሪያ በብሄር የተደራጁ ድርጅቶችን በኢትዮጵያ ጥላ ስር ወደ አንድነት የሚደረገው ጥረት መጎልበት እንዳለበት ገልፀዋል። አርበኞች ግንቦት 7 በውህደት ከተቋቋመ ጀምሮ ባሉት ሁለት ዓመት ስላከናወናቸው ተግባራትም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በቅርቡ ስለሚካሄደው የድርጅታችን አጠቃላይ ጉባዔም የሚሉት አለ፡፡ 
በመጨረሻም ለመከላከያ ሰራዊት አባላትና ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ ያስተላለፉት መልዕክት አለ፡፡ 
በማክሰኞ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ ፕሮግራማችን ይጠብቁ :: 

ኢሳትጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላ (ምን አለሽ መቲ) በኢትዮጵያ በአነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያለውን ነጋዴ እያጠቃ ያለው የቀን ገቢ ግብር በተጓዳኝ የህወሃት አባላትን የመጥቀምና የኤፈርት ካምፓኒዎች ተግባርና ሌሎችን ከስራ ውጭ የማድረግ ተልዕኮዓቸውን ከፕሮግራሙ ይከታተሉ.....