Sunday, November 19, 2017

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራርና የውጭ ጉዳዮች አስተባባሪ የሆኑትን አቶ ነዓምን ዘለቀን "ወቅታዊ የሃገራችንን ሁኔታ (አርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

በዛሬ የዕለተ ዕሁድ ህዳር 10 ቀን 2010 ዓ.ም ፕሮግራማችን
ትንታኔ መሰረት ያደረገ የፀጥታ ዕቅድ" የሚል ሰነድ ከወያኔ ሾልኮ ወጥቷል በዚህ ሰነድ ላይ በተዘረዘሩ በርካታ ርዕሶች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል ፡፡
በመጨረሻም ተባብረን ማድረግ ብንችል አገዛዙን መጣል፣ ከዚህ አፋኝ ስርዓት መላቀቅ እንችላለን ብለው ያመኑትንም ተናግረዋል ትከታተሉ ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡
www.patriotg7.org

Image may contain: 1 person, suit and beard

Friday, November 17, 2017

የጸጥታ ሀይሎች እና ማህበረሰብ በብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የተወሰኑ ውሳኔዎች በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የድህንነቱ መ/ቤት ፍላጎቶች ለማሳካት በሚል የቀረበ መሆኑ ታወቀ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች የህወሐት ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ሰርገው በመግባት ጥቃት ፈፀሙ፡፡ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ንጋት 10:55 ሲሆን ጎንደር አዘዞ ወታደራዊ ካምፕ በአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ጥቃት ተፈፀመበት ፡፡ ከመስከረም ወር 2010 ዓ/ም ጀምሮ ካምፑን ቀደም ሲል ከነበረው 24ኛ ክፍለ ጦር የተረከበው የ42ተኛ ክፍለ ጦር የጦር መጋዝን ንጋት ላይ እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ በተፈፀመው ጥቃት መጋዝኑ በከፊል የተቃጠለ መሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚያም የአየር መንገድ እና የጎንደር ከተማ እሳት አደጋ ደርሰው በከፍተኛ ርብርብ ሙሉ በሙሉ ከመቃጠል ሊድን ችላል ፡ ይህ ጥቃት ህዳር 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት ከካርቱም ወደ መቀሌ ነዳጅ ጭኖ ሲመጣ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን ይሄን ጥቃት በፈፀሙ ታጋዮች ላይ ለክትትል ወታደሮች ሲወጡ ነው የጦር መጋዝኑ ላይ ጥቃት የተፈፀመው ፡ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ተረኛ መኮነን የነበረው ምክትል መቶ አለቃ ደረጄ ጉደታ እና የበር ዘብ የነበረው ምክትል አስር አለቃ የኔሁን ጥላዬ በቁጥጥር ስር ውለው ሲታሰሩ በካምፑ ጭልጋ በር በተባለ ማማ ላይ የነበሩ ሁለት ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ተሰውረዋል፡፡
ምስል ከፋይል
Bilderesultat for አርበኞች ግንቦት 7

ESAT Special Interview with Prof Birhanu Nega Part 1 Nov 2017

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (በአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

የዛሬ የዕለተ አርብ ህዳር 08 ቀን 2010 ዓ.ም ፕሮግራማችን
ዜና .... 
ከዕለቱ ዜና በማስቀጠል፡-ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮና ለኢሳት አፋን ኦሮሞ እንዲሁም ለኢሳት የትግረኛ ፕሮግራም በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳዮች ላይ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ሶስተኛው ክፍል እናቀርባለን ፡፡ ትከታተሉን ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡

www.patriotg7.orgImage may contain: 5 people, people sitting

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች ከሱዳን ነዳጅ ጭኖ ይጓዝ በነበረ የህወሓት ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ፈፀሙ፡፡ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 12 :48 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ጓንግ ወንዝ ድልድይ ከመድረሱ በፊት 100 ሜትር ሲቀረው መታጠፊያ ቦታ ላይ በህወሓት ወታደሮች ከፊትና ከኃላ ታጅቦ ሲጓዝ በነበረ ነዳጅ በጫነ ቦቴ መኪና ላይ በተፈፀመ ጥቃት ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ አስከ ተጫነው ነዳጅ ሲወድም በአሽከርካሪው እና በሚያጅቡት ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ፡፡ ከአሁን ቀደም እንደሚታወቀው ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአወጀበት ወቅት "ቀይ ዞን" በማለት በአደገኛ ቀጠና ከፈረጃቸው ቦታዎች አንዱ ከጎንደር መተማ ፡ ሱዳን ያለውን መስመር ነው፡፡ በመሆኑም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከንጋት 12:00 አሰከ ቀን 11:00 ብቻ ተሽከርካሪዎች እንደሚያልፉ እና ከዚህ ሰዓት በኃላ አይደለም ማንኛውም ተሽከርካሪዎች ይቅርና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም በመንገድ አያልፉም ፡፡ በመሆኑም የህወሓት ወታደሮች አጅበውት ከሱዳን በኩል የመጣው ይሄ ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ ከነጋዴ ባህር ማደር ሲገባው ከዚያ እንደማያድር ቢመሽም እንኳን ጎንደር መግባት እዳለበት ነዳጁ ለአስቸኳይ ግዳጅ ስለተፈለገ ታጅቦ እደሚሄድ መረጃው የደረሳቸው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች ከጓንግ ወንዝ ባለው አቅጣጫ ደፈጣ በመጣል ይሄን በአጀብ ሊያልፍ የነበረን ወያኔ ለልዩ ግዳጅ ሊያውለው ያቀደውን ነዳጅ እስከነ ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ በማውደም በሹፌሩና በአጃቢ ወታደሮች ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይሄ ጥቃት በተፈፀመበት አካባቢ ውጥረት የነገሰ እና ፍተሻም በእጅጉ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እዳለ ወያኔ ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ ወደ ጎንደር ከተማ በሚያስገቡ 3 መግቢያዎች ላይ ኬላዎችን ማለትም ከሁመራና ከደባርቅ በኩል ወደ ጎንደር መግቢያ ፣ ከባህር ዳር በኩል ባለው መግቢያ እና ከመተማ በኩል ባለው መግቢያ ከፍተኛ ፍተሻዎችን እያደረገ ይገኛል ፡ይሄ የሆነበትም ምክንያት ወያኔ በህዝብ ስም የህወሓት ካድሬዎችን እና የእሱ ተላላኪ የሆኑ የብአዴን ካድሬዎችን "የሰላም ኮንፈረንስ" ብሎ የጠራውን ስብሰባ በጎንደር የሚያካሂድ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ወደ ከተማዋ ገብተው ጥቃት ይፈፅሙብኛል የሚል ስጋት በመኖሩ ነው ሲሉ የመረጃ ምንጮቻችን ገልፀውልናል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች እንዲሁም በደሴ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ይገኛል፡፡