Friday, November 17, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች ከሱዳን ነዳጅ ጭኖ ይጓዝ በነበረ የህወሓት ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ፈፀሙ፡፡ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 12 :48 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ጓንግ ወንዝ ድልድይ ከመድረሱ በፊት 100 ሜትር ሲቀረው መታጠፊያ ቦታ ላይ በህወሓት ወታደሮች ከፊትና ከኃላ ታጅቦ ሲጓዝ በነበረ ነዳጅ በጫነ ቦቴ መኪና ላይ በተፈፀመ ጥቃት ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ አስከ ተጫነው ነዳጅ ሲወድም በአሽከርካሪው እና በሚያጅቡት ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ፡፡ ከአሁን ቀደም እንደሚታወቀው ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአወጀበት ወቅት "ቀይ ዞን" በማለት በአደገኛ ቀጠና ከፈረጃቸው ቦታዎች አንዱ ከጎንደር መተማ ፡ ሱዳን ያለውን መስመር ነው፡፡ በመሆኑም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከንጋት 12:00 አሰከ ቀን 11:00 ብቻ ተሽከርካሪዎች እንደሚያልፉ እና ከዚህ ሰዓት በኃላ አይደለም ማንኛውም ተሽከርካሪዎች ይቅርና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም በመንገድ አያልፉም ፡፡ በመሆኑም የህወሓት ወታደሮች አጅበውት ከሱዳን በኩል የመጣው ይሄ ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ ከነጋዴ ባህር ማደር ሲገባው ከዚያ እንደማያድር ቢመሽም እንኳን ጎንደር መግባት እዳለበት ነዳጁ ለአስቸኳይ ግዳጅ ስለተፈለገ ታጅቦ እደሚሄድ መረጃው የደረሳቸው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች ከጓንግ ወንዝ ባለው አቅጣጫ ደፈጣ በመጣል ይሄን በአጀብ ሊያልፍ የነበረን ወያኔ ለልዩ ግዳጅ ሊያውለው ያቀደውን ነዳጅ እስከነ ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ በማውደም በሹፌሩና በአጃቢ ወታደሮች ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይሄ ጥቃት በተፈፀመበት አካባቢ ውጥረት የነገሰ እና ፍተሻም በእጅጉ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እዳለ ወያኔ ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ ወደ ጎንደር ከተማ በሚያስገቡ 3 መግቢያዎች ላይ ኬላዎችን ማለትም ከሁመራና ከደባርቅ በኩል ወደ ጎንደር መግቢያ ፣ ከባህር ዳር በኩል ባለው መግቢያ እና ከመተማ በኩል ባለው መግቢያ ከፍተኛ ፍተሻዎችን እያደረገ ይገኛል ፡ይሄ የሆነበትም ምክንያት ወያኔ በህዝብ ስም የህወሓት ካድሬዎችን እና የእሱ ተላላኪ የሆኑ የብአዴን ካድሬዎችን "የሰላም ኮንፈረንስ" ብሎ የጠራውን ስብሰባ በጎንደር የሚያካሂድ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ወደ ከተማዋ ገብተው ጥቃት ይፈፅሙብኛል የሚል ስጋት በመኖሩ ነው ሲሉ የመረጃ ምንጮቻችን ገልፀውልናል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች እንዲሁም በደሴ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ይገኛል፡፡

No comments:

Post a Comment