በይፋ ባልተገለጸ ሁኔታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀበት የሃረሪ ክልል በወታደራዊ መሪዎች እየተመራ ሲሆን፣ ወታደራዊ መሪዎቹ ሰሞኑን በተለያዩ ቀበሌዎች እየዞሩ ህዝቡን እና ካድሬዎችን ካነጋገሩ በሁወላ የውይይቱ ውጤት ነው ያሉትን ለክልሉ መሪ ለአቶ ሙራድ አብዱላሂ አቅርበዋል።
በክልሉ ያለው ችግር የመሪዎች ችግር መሆኑን የገለጸት ወታደራዊ ባለስልጣናቱ፣ የመሪዎች አለመግባባት ህዝቡን አሸፍቶታል ብለዋል። የደቡብ ምዕራብ እዝ ምክትል የኦሮፕሬሽን አዛዡ ጄኔራል አማረ፣ በገጠር የሚገኙ አንዳንድ ኦሮሞዎች ሸፍተው ጫካ የገቡ በመሆኑ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ብለዋል። ፕሬዚዳንቱን በሚወሰዱት እርምጃ ከጎናቸው እንደሚቆሙም አስታውቀዋል።
በኤረር ወረዳ ውስጥ ህገወጥ የጦር መሳሪያ የተበራከተ በመሆኑ ፣ ሰራዊቱ መሳሪያውን ለማስፈታት መዘጋጀቱንም አዛዡ ተናግረዋል። ጄኔራል አማረ ክልሉን በጣምራ የሚመሩትን የኦህዴድ አመራሮችን በክልሉ ውስጥ ችግር እየፈጠሩ እንደሆነና መከላከያ ከሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ጎን እንደሚቆም አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል በሁንደኔ ወረዳ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች በሃረሪ ክልል ባለስልጣናት እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰት በማንሳት ከክልሉ እንዲወጡ ያቀረቡት ጥያቄ መልስ ባላገኘበት ሁኔታ አካባቢውን በህግ ወደ ሃረሪ ክልል ለማጠቃለል አዲስ አዋጅ እየወጣ ነው።
ሁንደኔ ወረዳ ለሃረሪ ክልል በይሁንታ የተለገሰ መሆኑን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ በወረዳው የሚኖረው የኦሮሞ ህዝብ ባለፉት 26 ዓመታት በሃብሊ ባለስልጣናት ከፍተኛ ጭቆና ሲደርስበት መቆየቱን ተከትሎ የመብት ጥያቄዎችን አንስቷል። አሁን ደግሞ አካባቢውን በህግ ወደ ሃረሪ ክልል ለማስገባት አዲስ አዋጅ መረቀቁን ምንጮች ረቂቅ አዋጁን በማያያዝ ከላኩን መረጃ ለመረዳት ተችሎአል።
No comments:
Post a Comment