Tuesday, November 14, 2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከስልጣናቸው እንዲነሱ የእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት መጠየቃቸው ተሰማ

 በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙት የእንግሊዝና የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናት የልኡካን ቡድን በሀገሪቱ የተፈጠረው ያለመረጋጋት በአስቸኳይ መፍትሄ ካልተገኘለት ውሎ አድሮ የከፋ አደጋ እንደሚያስከትል ለኢትዮጵያው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ባለስልጣናት ማስጠንቀቃቸው ተሰማ፡፡የታሸጉ ቆዳ ፋብሪካዎች እንዲከፈቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዘዙ
በተለይ የእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት ከአቶ ጌታቸው አሰፋ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ሀላፊ ጋር ባደረጉት ምክክር ሀገሪቱ የገባችበት ችግር ዋንኛው ምክንያት ጠንካራና ተጻእኖ ፈጣሪ ጠ/ሚኒስትር ማጣትና ጠ/ሚኒስትር ሀ/ማርያም የተፈጠረውን ሁኔታ መቆጣጠርም ሆነ በተለያዩ አካላት ላይ ተጽእኖ ፈጠሮ ሀገሪቱን መምራት የተሳናቸው እንደሆኑ መጠቆማቸውን ኢሳት የጸጥታ ሀይሎችና ማህበረሰቡ በሚለው የዜና ፕሮግራሙ አስደምጧል።
በምትካቸውም ጠንካራ የፖለቲካ መሪ መሆን የሚችል ሰው
ማስቀመጥ አስፈላጊ መሆኑን እንዲሁም የጠቅላይ ሚንስትር ቦታውን ከሳቸው የሚረከበው ሰው ከሌላ ብሄር እንዲሆን
ከእንግሊዞቹ ጥያቄ መቅረቡም በፕሮግራሙ ተዘግቧል።
አቶ ጌታቸው በበኩላቸው በጉዳዩ ላይ እየሰሩበት ያለ ጉዳይ
ስለመሆኑና ይልቁንም ለቦታው ያጩት ሰው ስለ መኖሩ፤
ያጩትንም ሰው ለረጅም ጊዜ የሚያውቋቸውና አብረውም የሰሩ መሆኑን ተናግረው የታጨውን ሰው ስምን ግን ከመግለጽ መቆጠባቸውን ዜናው ያስረዳል፡፡

አቶ ጌታቸው ከእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት የቀረበላቸውን ጥያቄና እሳቸውም ያጩትን አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ለስልጣን የማብቃት ስራን ተግባራዊ ለማድረግ ይቻላቸው ዘንድ ከእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት ጠንካራ ድጋፍ እንደሚሹ የጸጥታ ሀይሎችና ማህበረሰቡ የተባለው ፕሮግራም በዝርዝር አስደምጧል ።
የህወሀት ባለስልጣናትን እንዲሁም የጦር ጀነራሎችን
በማግባባትና ለተግባራዊነቱ ተባባሪ እንዲሆኑ ለማድረግ
የአሜሪካ መንግስት የማግባባቱንና የማደራደሩን ስራ እንድትሰራ እንግሊዝ ግፊት እንድታደርግ አቶ ጌታቸው አጠብቀው መጠየቃቸውን በፕሮግራሙ ተደምጧል።
በህወሃት ድርጅት ውስጥ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያምን
በመቀየሩ ሀሳብ ላይ ቢስማሙም በሚተካው ሰው ላይ እስካሁን መስማማት ያለመቻላቸወም በዜናው ተዘግቧል፡፡

No comments:

Post a Comment