በባህርዳር ከተማ በ ዳግማዊ ዮሃንስ ሆቴል ላይ የቦንብ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ አቶ አለምነው መኮነን በከተማዋ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርስበት ምክንያት ምንድነው በማለት የደህንነት አባላቱን ሰብስበው ጥያቄ ማቅርባቸውን የገለጹት ምንጮች፣ ችግሩ ያለው በደህንነቱ አባላት ላይ ነው በማለት አንዳንድ አባላቱን በማንሳት ሌሎችን ሹመዋል።
አቶ አለምነው “የአማራ ደህነት ቢሮ ብዙ መዋቅራዊ ለውጥ ቢደረግበትም ምንም ለውጥ ማምጣት አልቻለም፣ በዚህ ከተማ ፀረ ሰላም ሀይሉ በተደጋጋሚ እንደልቡ እየፈነጨበት ነው፣ የዚህ ከተማ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ነው” በማለት የክልሉን የደህንነት አባላት አጥብቀው የወቀሱ ሲሆን፣ እርሳቸውና አስተዳደራቸው በደህንነት ተቋሙ ላይ እምነት ማጣታቸውን ተናግረዋል።
በአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳይ ቢሮ የመረጃ ክፍል ሃላፊ የነበረውን አቶ አየለ አናውጤን በማንሳት በምትኩ አቶ የማነ ታደሰ የተባለ የህወሃት አባል ሀላፊ አድርገው መሾማቸውን ምንጮች ገልጸዋል። አቶ አለምነው በቅርቡ አቶ ፍሰሃ ወ/ሰንበትን በማንሳት አቶ እዘዝ ዋሴን የክልሉ የደህንነት ቢሮ ሀላፊ አድርገው ሾመው ነበር። አቶ አለምነው በደህንነት መዋቅሩ ውስጥ ያሉ የአማራ ተወላጆችን እያስወጡ ቦታውን ህወሃቶች እንዲይዙት እያደረጉ ነው የሚል ከፍተኛ ወቀሳ እየቀረበባቸው ነው።
No comments:
Post a Comment