የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ተኛ ዙር 3ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ተኛ መደበኛ ጉባዔ በትናንትናው ዕለት በባህርዳር የተጀመረ ሲሆን ከጅምሩ አፈ ጉባኤው ከአቀረቡት አጀንዳ በተጨማሪ የምክር ቤት አባላት በአጀንዳነት መያዝ አለባቸው በማለት በርካተ ርዕሰ ጉዳዬችን በማንሳታቸው በተለይም በኢትዮ ሱዳን ድንበር ፡ በትግራይ እና በሰሜን ጎንደር በኩል ያለው የአማራ ድንበር ፡ በትግራይ እና በወሎ በኩል ያለው የአማራ ደንበር ፡ በእኩል ተጠቃሚነት በኩል ከኢንዱስትሪዎች እና ኢንቨስትመንቶች ፡ እንዲሁም ከህወሐት የበላይነት ወዘተ ጋር የመሳሰሉት በአጀንዳነት ሊያዙ ይገባል የሚሉ ጉዳዬች በመነሳታቸው በስብሰባው አዳራሽ ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቷል ፡፡ ከዚያም የብዓዴኑ ሹም ገዱ አንዳርጋቸው ጣልቃ በመግባት መጀመሪያ በቀረቡት የስራ ክንውኖች ላይ እንወያይና በቀጣይ በቀረቡት ነጥቦች እንመክራለን በሚል በሰነዘረው ሀሳብ ስብሰባው መጀመር ከነበረበት ሰዓት እጅግ ዘግይቶ ተጀመረ እንዲያም ሆኖ በትምርት ዙሪያ በቀረበው ሪፖርት ላይ አለመግባባት በመፈጠሩ ፡ ይሄን መረጃ ለሌላ ጊዜ እናቆየውና በምክር ቤቱ አባላትና በአለምነው መኮነን መካከል ግጭት ወደ ተፈጠረበት መረጃ እንለፍ በማለት ተስማምተው ፡ የምክር ቤቱ የቀን ውሎ እንዳበቃ 12:00 ሰዓት ሲሆን ከሰሜን ጎንደር ዞን ፡ ከሰሜን ወሎ ዞን እና ከዋግ ህምራ ዞን የመጡትን የምክር ቤት አባላት ከአዳራሹ እዲቆዩ በማድረግ አፈ ጉባኤውና ገዱ አንዳርጋቸው ከመድረኩ ወርደው በመድረክ ወንበር ላይ አለምነው መኮነን እና ምግባሩ ከበደ በብአዴን ውስጥ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ወኪል ሆኖ እየሰራ ያለው ተቀመጡ ፡፡ ከዚያም አለምነው እናንተን ነጥለን ወደ ኃላ እድትቆዩ ያደረግነው በጥዋቱ የምክር ቤት ጉባኤ መክፈቻ ላይ ከድርጅታችን ብአዴን አቋም ውጭ የሆኑ ሀሳቦችን ስታነሱ ሰምተናል ፡ እናንተ ወደ እዚህ ምክር ቤት የመጣችሁት ብአዴንን ወክላቹሁ እና ህዝቡም ለብአዴን ድምፅ ሰጥቶ ስለመረጣቹሁ ነው በመሆኑም በድርጅታችን የዲስፕሊን መመሪያ መሰረት ነው ልትንቀሳቀሱ የምትችሉት ፡ በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል ባሉ ድንበሮች የነበሩ ችግሮች ሁለቱ ድርጅቶች እና የአካባቢው ህብረተሰብ ተወያይቶ መፍትሔ የሰጠበትን አሁን ከዚህ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ማንሳት ተገቢ አይደለም ፡ ከሱዳን ጋር ያለውም ቢሆን ፀረ ሰላም ኃይሎች ከሚያራግቡት ውጭ ነው ሰላማዊ ነው ወዘተ እያለ እነዚህን የምክር ቤት አባላት ለማሳመን ቢሞክርም የምክር ቤት አባላቱ ንግግሩን አቋርጠው አንድ የምክር ቤት አባል ድንበርን በተመለከተ የትኛው ህዝብ ነው የተወያየውና የተስማማው ? ህወሓት ይዞት የቀረበውን አጀንዳ ካልተቀበልንም በአርበኞች ግንቦት ሰባት ተፈርጀን በአሸባሪነት እንጠየቃለን ፡ በዚህ ሁኔታ የሁለቱ ድርጅቶች ግንኙነት መሻከር የለበትም ፡ወዘተ... ተብሎ ማስፈራሪያ ቢሰጥም ይሄን ማስፈራሪያ ወደ ጎን በመተው የተከራከሩትን በማሰር በኃይል የተሰጠ ነው በማለት ተናገሩ ሌላም የምክር ቤት አባል በወሎ በኩል ምን መፍትሔ ሰጥታቹሁ ነው እንደዚህ የምትሉት ? እኛ እኮ ከህዝብ ጋር ነው ያለነው ህዝቡ የሚለውን ነገር በሙሉ በቅርበት የምንሰማው እኛ ነን በማለት ሲናገሩ ጉዳዩ ወደ ስድብና ንትርክ ሲያመራ ምግባሩ ከበደ ደግሞ " ይሄ አይነት ሀሳብ ከናንተ የመጣ አይደለም ሁላቹሁም የምትሉት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አሸባሪው ቡድን ሀሳብ እና የትምክህተኞች ሀሳብ ነው ይሄ ደግሞ በህግ ያስጠይቃል " በማለት ሲናገር እኛ የምንለውን እናውቃለን እስከ መቼ ባሪያዎች ሆነን እንቀጥላለን ማስፈራራቱን እናየዋለን በማለት ቀድሞም ወደ ኃላ ቅሩ ብላቹሁ እኛን ነጥላቹህ ማስቀረታችሁ ህገ ወጥ ነው እኛ ተጠሪነታችን ለመረጠን ህዝብ እንጂ ለናንተ አይደለም በማለት መድረኩን ረግጠው ወጥተዋል ፡ አሁን ባለው ሁኔታ ውጥረቶች በርትተዋል፡፡
No comments:
Post a Comment