Monday, November 27, 2017

ህወሀት ጉልቻ እየቀያየረ ነው። (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)


የፊት ለውጥ ይዞ ሊመጣ መሆኑ ታውቋል። አዜብ መስፍን ባፋንጉሎ ተብላለች። የኢትዮጵያን ህዝብ ደም የመጠጠው ኢፈርት የተሰኘው ድርጅት የንትርኩ ማጠንጠኛ ይመስላል። እነአዜብና በየነ ምክሩ ከዚሁ ድርጅት ጋር በተያያዘ አይናቸው ደም በለበሰባቸው በእነስብሃት ነጋ ብጫና ቀይ ካርድ ተሰጥቷቸዋል። እነስብሃት ለጊዜው በለስ ቀንቷቸዋል። የመለስ ሌጋሲን ከመለስ ጋር እንዲቀበር የፈለጉት እነስብሃት የሌጋሲውን አቀንቃኞች በጠረባ እያሏቸው ነው። ስብሰባ ሳይጠናቀቅ መግለጫው መቅደሙ ግን ገና ጦርነቱ ያላበቃ መሆኑን ያሳያል።
እነኣዜብ ኢፈርትን ለነስብሃት አስረክበው ቤታቸው ይገባሉ? የመለስ ዜናዊ አምላኪ የሆነው ሳሞራ የኑስ ምን ብሎ ይሆን? ኢፈርትን የተቆጣጠረ ሻምፒዮን ይሆናል። የኢኮኖሚ ጡንቻ የሚሰጠው ኢፈርት ለፖለቲካው የበላይነት የጀርባ አጥንት መሆኑን አቦይ ስብሃት ልቅም አድርገው ያውቁታል። እናም የመለስን ሌጋሲ ከነአስጠባቂዎቹ መንግሎ ለመጣል መንገዱን በኢፈርት ጀምረውታል። በፖለቲካው ቀጥለዋል። እነአዜብ እጃቸውን አጨብጭበው ኢፈርትን ካስረከቡ የመልስን ሌጋሲ ብቻ ታቅፈው ይቀራሉ።
ፈረንጆቹ the bottom line ይላሉ። ዋናው ጉዳይ እንደማለት ነው። እናም ዋናው ጉዳይ የአዜብ መወገድና የስብሃት ማንሰራራት አይደለም። ጉልቻ ቢቀያየር ትርጉም የለውም። ወጥ አያጣፍጥም። ኢትዮጵያን አይቀይርም። ሌሎችንም ቱባ ባለስጣናት በማባረርና በእስር የሚገኙ ተቃዋሚዎችን በመፍታት ይህቺን የምጥ ጊዜ ለመሻገር ህወሀት ተዘጋጅቷል። ፊት በመቀየር፡ ጉልቻ በመለወጥ ህወሀት የሚድን ከመሰለው ተሳስቷል። ህወሀት ከነግሳንግሱ፡ ከነኮተቱ፡ ከራስ ጠጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ፡ አንድም ትራፊ ሳያስቀር ካልተወገደ በቀር ለውጥ አይኖርም። የኢትዮጵያ ህዝብ የሚናፍቀው ያንን ነው።Image may contain: 1 person

No comments:

Post a Comment