Friday, December 19, 2014

በዛሬው የባህርዳሩ ተቃውሞ 3 ሰዎች ሲገደሉ 7 ሰዎች መቁሰላቸው ተሰማ

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ ጠዋት ባህርዳር ከተማ ላይ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ፖሊስ በኃይል ለመበተን የሃይል እርምጃ እየወሰደ ሲሆን ህዝቡ በብዛት ተቃውሞውን እየተቀላቀለ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ለዘ-ሐበሻ እንደደረሱት መረጃዎች ከሆነ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የ3 ወጣቶች ህይወት ያለፈ ሲሆን ሌሎች 7 የሚሆኖ ወጣቶች ቆስለዋል:: የሟቾችና ቁስለኞች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::
9783_596573470488802_1311708396556689267_n
በሌላ በኩል ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው በአሁኑ ወቅት ከቀበሌ 10 አባይ ማዶ ያለው መንገድ ተቃውሞውን በተቀላቀለው ህዝብ የተዘጋ ሲሆን ወደ ጎንደር የሚወስደው መንገድም መዘጋቱ ታውቋል፡፡ የቀበሌ 8፣ 10ና 11 ነዋሪዎች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞውን እየተቀላቀሉ ነው ተብሏል፡፡ የአፈ ጉባኤ ጽ/ቤት አካባቢም በርካታ ህዝብ የተገኘ ቢሆንም ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት የሉም እንደተባሉ ሰልፈኞቹ ገልጸዋል::



ከዚህ ዜና በፊት ዘ-ሐበሻ እንደዘገበቸው የተቃውሞው መነሻ ባህርዳር ከተማ ውስጥ 04 ቀበሌ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን የጥምቀት ታቦት ማደሪያ ለባለሀብት ይሰጣል መባሉን ተከትሎ ነው::

No comments:

Post a Comment