ጉልበት አንድቀን ይደክማል ዘላለም በጉልበት መግዛት አይቻልም የብዙ ጉልበተኞች ጉልበት ሲሠበር አይተናል የሩቁን ትተን የትላንቱን ብንመለከት ጥሩ ትምህርት መቅሠም ይቻላል ከጋዳፊ , ከሙባረክ መማር ይቻላል የኛዎቹ ገዥዎች ለመማር የተዘጋጁ አይመስልም ሠነፍ ከውድቀቱ ይማራል እንዲሉ ኢሀዴግ ከማን ታሪክ እንደሚማር አልታወቀም
ህውሀት መራሹ አገዛዝ ከሌሎች አንባገነኖች ልዩ የሚያደርገው ከሌሎች አለመማሩ ብቻ ሣይሆን ሆን ብሎ ይሁን በድንቁርና ከህዝብ የሚጣላበት ጉዳይ መፈለጉ ነው ባለፉት ጥቂት አመታት ከሙስሊም ማህበረሰብ ጋር አያገባው ገብቶ ሲጣላ ከረመ አሁንም ፀቡን አጠናክሮ ቀጥሏል በክስቲያኑ ማህበረሠብ ፀብ የጀመረው ገና ጉልበታቸው ሣጠና ከጫካ እንደመጡ ቢሆንብ በእድሜ ብዛት መማር ሣይሆን ፀቡን አክርረው ቀጥለዋል ለዚህም ማሣያ የሚሆነን ዛሬ ከባህር ዳር የሠማነው ዜና በቂ ይመስለኛል የባህር ዳር ህዝብ መብቱን አሣልፎ የሠጠ አይመስለኝም ካካባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ትግሉ የሚጠይቀውን ዋጋ እየከፈሉ ነው በዚህ አጋጣሚ የባህርዳርን ህዝብ በርቱ ማለት ያሻልና በርቱ ልንላቸው ይገባል ትግሉንም ማገዝ ይገባል ነገ እኛ ቤት መምጣቱ አይቀሬ ነውና
No comments:
Post a Comment