December 19, 2014
(ነገረ-ኢትዮጵያ) ባህርዳር ከተማ ውስጥ 04 ቀበሌ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን የጥምቀት ታቦት ማደሪያ ለባለሀብት ይሰጣል መባሉን ተከትሎ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን በማሰማት ላይ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጸዋል፡፡
(Click here to watch video) የባህርዳር ህዝብ ተቃውሞውን እየተቀላቀለ ነው
• አምስት ሰዎች ሲቆስሉ ሁለት ሞተዋል
(ነገረ-ኢትዮጵያ) ዛሬ ጠዋት ባህርዳር ከተማ ላይ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ፖሊስ በኃይል ለመበተን ጥረት እያደረ ቢሆንም ህዝቡ በብዛት ተቃውሞውን እየተቀላቀለ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሌሎች አምስት ያህል ወጣቶች እንደቆሰሉ ተገልጾአል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከቀበሌ 10 አባይ ማዶ ያለው መንገድ ተቃውሞውን በተቀላቀለው ህዝብ የተዘጋ ሲሆን ወደ ጎንደር የሚወስደው መንገድም መዘጋቱ ታውቋል፡፡ የቀበሌ 8፣ 10ና 11 ነዋሪዎች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞውን እየተቀላቀሉ ነው ተብሏል፡፡ የአፈ ጉባኤ ጽ/ቤት አካባቢም በርካታ ህዝብ የተገኘ ቢሆንም ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት የሉም እንደተባሉ ገልጸውልናል፡፡
————————-
ምንጮቹ እንደገለጹት እጅግ በርካታ ህዝብ አደባባይ የወጣ ሲሆን፣ ሰልፈኞቹ በእምነታቸው እየተደረገባቸው የሚገኙትን ጣልቃ ገብነቶችና ሌሎቹንም ስርዓቱ እየፈጠራቸው የሚገኙትን ችግሮች የሚቃወሙ መፈክሮች እያሰሙ ይገኛሉ፡፡
የአማራ ክልል አስተዳደር የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያን የተጠራው ተቃውሞ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከታቦት ማደሪያው 9 ሜትር ገብቶ መንገድ እንዲሰራ እንዲሁም ቀሪው ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች እንዲሰጥ አስተዳደሩ ማዘዙን ተከትሎ ታቦት ማደሪያውን ከነገ ህዳር 10/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሊፈርስ እንደነበር መረጃው የደረሳት ቤተ ክርስቲያን ለህዝበ ክርስቲያኑ አስቸኳይ ጥሪ ማስተላለፏ ታውቋል፡፡
ህዝቡም ‹‹በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተገናኝተን በእግዚያብሄር ስም በአስቸኳይ ጠርተንዎታል›› በሚል በቀረበለት ጥሪ መሰረት ዛሬ ጠዋት ተቃውሞውን የጀመረ ሲሆን አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ተገልጾአል፡፡ ህዝቡ ቀበሌ 10 በሚገኘው አዲሱ ምክር ቤት እንዲሁም በዚሁ ቀበሌ በሚገኘው የቀድሞው ምክር ቤት በመገኘት ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል፡፡ በተለይ በአዲሱ ምክር ቤት ተገኝቶ ተቃውሞውን እያሰማ የሚገኘውን ህዝብ በኃይል ለመበተን ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
No comments:
Post a Comment