የመንግስት የ11 በመቶ የእድገት ፕሮፓጋንዳ ዜጎችን ከስደት አንዳልታደጋቸው አንደነት ገለጸ
ፓርቲው በቅርቡ በየመን የባህር ዳርቻ ያለቁትን ከ70 በላይ ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አደጋው ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው መኖር አለመቻላቸውንና ሰርክ የሚለፈፈው የ11 በመቶ እድገት ዜጎችን ከስደትና ከመከራ ሊታደጋቸው እንዳልቻለ የሚያሳይ ነው ብሎአል።
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በዜጎች ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጾ፣ ስደትና እልቂት ከዚህ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ህዝቡ ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለውና ለስደት የዳረገውን ስርዓት በመታገል ህዝባዊ የሆነ መንግስት ማቋቋም እንደሚገባው እናምናለን ብሎአል።
መፍትሄው ስደት ሳይሆን እዚሁ አላሰራ ያለውንና ነፃነት ነጣቂውን መንግስት በመፋለም ስር ነቀል ሀገራዊ ለውጥ እንዲመጣ መታገል ነው በሚል ለህዝቡ መልእክት አስተላልፏል።
No comments:
Post a Comment