Friday, December 12, 2014

ESAT

የተቃውሞ ሰልፍ በማድረጋቸው ብቻ ታስረው የነበሩ 9 ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ተፈቱ
ባለፈው ህዳር 27 በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሲዘጋጁ በፖሊስና በደህንነቶች ቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የ9 ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ከእስር የተለቀቁ ሲሆን፣ ብዙዎቹ በእለቱ በደረሰባቸው ድብደባ ከመጎዳታቸውም በተጨማሪ በእስር ቤት ውስጥ የነበራቸው አያያዝ አስከፊ እንደነበር ታውቋል።


የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባል የሆነው ይድነቃቸው ከበደ ደህንነቶች ወደ እስር ቤት በተደጋጋሚ እየሄዱ ከማን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ይጠይቁ እንደነበር፣ የኢሜል፣ የትዊተርና የፊስ ቡክ የሚስጢር ቁልፋቸውን እንዲሰጡ ያስገድዷቸው እንደነበር ገልጿል። እስረኞቹ ብሄራቸውን እንዲናገሩ ሲጠየቁ ኢትዮጵያዊ ብለው በሚመልሱበት ወቅት ከፍተኛ እንግልት ይደርስባቸው እንደነበር ይደናቀቻው ተናግሯል። ( )
በእስር ቤት ቆይተው ከተፈቱ የ9 ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት ጋር የምናደርገውን ቃለምምልስ በተከታታይ እንደምናቀርብ ለመግልጽ እንወዳለን።

No comments:

Post a Comment