Tuesday, May 19, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አበባ ውስጥ ስኬታማ ቅስቀሳ አደረገ!
ግንቦት 9/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ላይ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ የተከለከለው ሰማያዊ ፓርቲ በዛሬው ቀን በአዲስ አበባ ስኬታማ የመኪና ላይ ቅስቀሳ አካሄደ፡፡ ሰማያዊ በሰባት መኪናዎች በመገናኛ፣ አራት ኪሎ፣ ስድስት ኪሎ፣ ጊዮርጊስ፣ ፒያሳ፣ አስኮ፣ መሳለሚያ፣ አውቶቡስ ተራ፣ መርካቶ፣ ሜክሲኮ፣ ጨርቆስ፣ ጎተራ፣ ወሎ ሰፈር፣ ቦሌ፣ መስቀል አደባባይና ሌሎች የአዲስ አበባ ክፍሎች ላይ ስኬታማ የመኪና ላይ ቅስቀሳ አድርጓል፡፡
አዲስ አበባ ውስጥ ሰባት መኪናዎች በአንድ መስመር ሆነው ሲቀሰቅሱ የዋሉ ሲሆን በተመሳሳይ በለገጣፎና ሰንዳፋ ከተሞችም ቅስቀሳ ተደርጓል፡፡

No comments:

Post a Comment