Tuesday, May 19, 2015

የህወሓት አየር ኃይል ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያደርገው ጉዞ መሰረዙ ተሰማ

  • 567
     
    Share
ethiopian airforce
ምኒልክ ሳልሳዊ ዘንደዘገበው
የህወሓት አየር ኃይል ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያደርገው ጉዞ መሰረዙ ተሰማ፡፡በበረራ፣ ጥገና፣ ድጋፍ ሰጪ፣ ዘመቻና አስተዳደር ከ200 በላይ አባላቱን በከፍተኛ ወጪ ለ6 ወራት ሲያሰለጥን የባጀው አየር ኃይል የሰላም ማስከበሩ ተልዕኮ ወደሚከናወንበት ደቡብ ሱዳን ሊጓዙ የተመረጡት መንገደኞች ከየአየር ምድቦቻቸው ተነስተው ደብረ ዘይት ከከተቱ በኋላ ጉዞው ድንገት ተዘርዟል፡፡
ጉዞው የተሰረዘባቸው ምክንያቶች በአባላትና አባላት፣ በአባላትና አመራሮች እንዲሁመም በአመራሮችና አመራሮች መካከል አለመተማመን በመስፈኑ፤ ያለመጠን ስር ሰዶ የተንሰራፋው ጎሰኝነት ተባብሶ በትግርኛ ተናጋሪ የህወሓት ሰዎች መካከልም ውቅሮና አዲግራት ወደሚሉ የመንደር ቡድንተኝነት ቁልቁለቶች በመውረዱ፤ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ አሁንም አብራሪዎች ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችን ይዘው ሊኮበልሉ ይችላሉ ከሚል ስጋት በመነጨ፣ ከፍተኛ በሆነ
የአቅም ማነስ ችግር፤ ከምርጫው ጋር በተያያዘና ብረት ያነሱ የነፃነት ኃይሎች ጦርነት ይከፍታሉ ተብሎ በመሰጋቱ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘው አየር ኃይል ከዚህ በፊት በ2005 ዓ.ም በብቃት ማነስ ምክንያት ከዳርፉር ተባሮ የሰላም ማስከበር ተልዕኮውን ሳያሳካ ጓዙን ጠቅልሎ ውርደት በመከናነብ መመለሱ አይዘነጋም
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41482#sthash.XaTVZqf3.dpuf

No comments:

Post a Comment