Friday, May 8, 2015

ወያኔዎች የፈሩትን አይቀሬ ህዝባዊ መዓበል ሳያውቁት እያፋጠኑት ይገኛሉ፤፤፤ የለውጥ ሃይሎችን አፍሶ በማሰር እና በማሳደድ ስር ነቀሉን የለውጥ አብዮት ማስቆም አይቻልም

;;; ወያኔዎች የፈሩትን አይቀሬ ህዝባዊ መዓበል ሳያውቁት እያፋጠኑት ይገኛሉ፤፤፤
የለውጥ ሃይሎችን አፍሶ በማሰር እና በማሳደድ ስር ነቀሉን የለውጥ አብዮት ማስቆም አይቻልም
በሃገራችን ውስጥ ለይስሙላ በወያኔ የተጠራውን ምርጫ በመንተራስ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያጣው የወያኔ ስርአት የለውጥ ሃይሎችን እያፈሰ በማሰር እና በማሳደድ ላይ መሆኑ ባለፉት ሳምንታት እየተመለከትን ነው::የወያኔ አምባገነን ጁንታ በጠራው የጸረ አይሲስ ሰልፍ አሳቦ የተቃዋሚ ሃይሎች አባላትን በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ የለውጥ ሃይሎችን እንዲሁም የተለያዩ የለውጥ ፈላጊ ሃይሎችን ከየመንገዱ እየለቀመ እያፈሰ በማሰር ከአዲስ አበባ ውጪ በሚገኙ የማጎሪያ ካምፖች እያከማቸ ይገኛል:እንዲሁም መንግስታዊ ሽብርተኝነትን በመሸሽ የሚሰደዱ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ በገሃድ እየታየ ነው::


አዲስ አበባ እና በክፍለ ሃገር ከተሞች ምርጫውን ተከትሎ ግርግር ያነሳሉ ሕዝባዊ አመጽ ይመራሉ ያስተባብራሉ የተባሉ ወጣቶች ታፍሰው የታሰሩ በአውቶብስ እና በጭነት መኪና ተጭነው ከየእስር ቤቱ ከከተሞች ክልል ውጪ ባሉ የማጎሪያ ካምፖች በመውስድ ላይ መሆኑን ሲታወቅ ገና ያልተጫኑ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች በየእስር ቤቱ እንደሚገኙ ጉዳዩን እየተከታተሉ የሚገኙ የገለጹ ሲሆን የለውጥ ሃይል የሆኑ ወጣቶችን አፍሶ አስሮ እና አሳዶ ስር ነቀል የሆነውን የለውጥ አብዮት ማስቆም እንደማይቻል ወያኔዎች በፍጹም አልተረዱትም::እንዲሁም ከምርጫው ጋር በተያያዘ አፈሳውን እና መታሰሩን በመፍራት የተለያዩ ክፍለሃገር ነዋሪዎች ወደ ጎረቤት ሃገሮች እየተሰደዱ መሆኑ ከየአከባቢው የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ::
ምርጫውን ተከትሎ የስል ነቀል አብዮት አመጽ ያሰጋው ወያነ ህዝቡ አንድነቱን በማሳየት በአደባባይ ተቃውሞውን መግለጹ ከፍተኛ ስጋት ላይ እንደጣለው ራሱ እየመሰከረ ባለበት ባሁኑ ወቅት የምርጫ ካርዶችን አምጡ በማለት በማስገደድ ላይ ይገኛል::ወያኔ ማንም እንደማይመርጠው በማወቁ ያለው እድል የመሳሪያ ሃይል ተጠቅሞ በአንድነት የተነሳበትን ሕዝብ ማዳከም ሌላው አላማ ቢሆንም አንድ ለአምስት ብሎ ከዚህ ቀደም ያደራጀው እንዳልሰራለት እና አሁንም በሌላ መንገድ ያንኑ አንድ ለአምስት የሚለውን አደረጃጀቱን ለምርጫው ለመጠቀም እየሰራ መገኘቱ የለውጥ ሃይሎች የትግል ውጤት ምን ያህል እንዳፍረከረከው በተግባይ እየታየ ነው::ይህንንም የለውጥ ሃይሎች እንቅስቃሴ በመስጋት በከፍተኛ ደረጃ ወጣቶችን በማፈስ በማሰር እና በማሳደድ ለማሸማቀቅ ቢሞክርም ቀሪው የህብረተሰብ ክፍል ከንፈሩን በመንከስ ወያኔን ሊበቀለው በዝግጅት ላይ መሆኑን በተግባር አንድነቱን አጠናክሮ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል::ወጣቱን ሃይል በማሰር እና በማሳደድ ስር ነቀሉን የለውጥ አብዮት ማስቆም አይቻልም:

No comments:

Post a Comment