Saturday, May 16, 2015

ኦሮሞና ኢትዮጵያዊነት
ኦሮሞነት ማለት ደግነት ነው፤ ኦሮሞነት ማለት ውሀ አጠጡኝ ላለ ወተት የሚሰጥ ተጠልቆ ያማይነጥፉ ፍቅር ማለት ነው። ኦሮሞን ከውጭ መጣ የሚሉ የታሪክ ጸሀፊዎች ነን የሚሉ ደናቁርትና ጠባብ ፖለቲከኞች ያስገርሙኛል። ኦሮሞ ከየትም አልመጣም፤ የትም አልሄደም። ጥንተ መሰረቱ ከኩሽ መገን የሆነ የደጋጎች መገኛ ነው። ኦሮሞ እንደማንኛውም ህዝብ ሁሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል ሲንቀሳቀስ፥ ባህሉን ሲያጋራ፥ የወገኖቹንም ባህል ሲላበስ የኖረ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ነው። ኦሮሞነት ማለት ኢትዮጵያዊነት ነው።

ታላቁ መጽሀፍና ታሪክ እንደሚያስረዱት በታሪክ ቀደምቶቹ የጥበብንና የሳይንስን ፋና ከለኮሱት ፈር ቀዳጆች መካከል ኢትዮጵያዊያኖቹ ኩሻይቶችና የካም ልጆች ፤ የጥንታዊ ከተሞችና የሥልጣኔ ሕይወት (ኑሮ) መስራቾች እንደሆኑ በደማቅ ቀለም ተጽፋል። በኮሎምቦስ ጊዜ የሕንድን አስገራሚ ነገሮችን አውሮፓውያን ያዩዋቸው ውድ ምርቶች፤ የተመኟቸው የባቢሎን የንግድ እቃዎች፤ የኤሽያ ቅድመ ታሪክ ስልጣኔዎች ሁሉ ከኢትዮጵያ ኩሻይቶችና ከካማውያን የፈለቁ ተስልጣኔ ውጤቶች ናቸው፡፡ በቀድሞው ዘመን የነዚህ ዘሮች የተሳካ ውጤት የተገኘው በህብረታቸው ነው፡፡ የኩሽ ነገዶች እውነተኛው የዴሞክራሲ ከፍተኛ ደረጃ በገዳ ዘመን ደርሰዋል፡፡
የካምና የኩሽ እጆች ተዐምረኛ የሆኑ ግንቦች አነጹ፤ታላላቅ ሃይቆችን ገደቡ፤እስከ ዓመታት ሊዘልቁ የሚችሉ መንገዶችን ቀደዱ፡፡ የጥንቱ ማህደር የሚያሳየው ይህን የማይታበል የአብሮነትና ያጋራ እውነታ ነው፡፡ ጠባውብ ፖለቲከኞችና ዘመናዊ ጸሃፍት ላይ ላዩን ብቻ ነው የሚለክፉት አለያም እነዚህን እውነታዎች አልተገነዘቧቸውም፤ ካልሆነም አውቀው ችላ ብለው ትተዋቸዋል፡፡ የታሪክ ቅርስ ተመራማሪዎች ማስረጃዎቹን ከመቃብር እየቀሰቀሷቸው ነው፡፡ የሰው ዘር አጥኚዎች መሰረታቸውን ይፋ ያደርጋሉ፤ ታሪክ ግን ጊዜ ያለፈበት፤ የባረቀበትን ጽንሰ ሃሳብ ለመለወጥ አሻፈረኝ ብሏል፡፡
በዘመኑም ኢትዮጵያ ኦሮሞ፤ ኦሮሞ ኢትዮጵያ ነው። ኦሮሞ የሌለበት የኢትዮጵያ አሻራ ሊኖር አይችልም፤ አይኖርምም። ያለ ጥላሁን ገሰሰ የኢትዮጵያ ዘፈን ምንድን ነው? ያለ ጸጋየ ገብረ መድህን ጽሁፍ የኢትዮጵያ ስነጽሁፍ በሁለት እግሩ እንዴት ይቆማል? ያለ ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ምን ኩራት አለው? በአገሩ ጉዳይ ቀልድ የማያውቅ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ኦሮሞ-ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ-ኦሮሞ!Q

No comments:

Post a Comment