Wednesday, October 18, 2017

አሁን የደረሰን ዜና ፦ በገብረጉራቻ ተቃውሞ ተባሶ ቀጥሏል፡፡ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

ዛሬ ማምሻውን በርካታ ቤቶች እየተቃጠሉም ይገኛሉ ፡፡የመንግስት ተሸከርካሪዎችና የስርአቱ ደጋፊ የሆኑ ባለሃብት ንብረቶች እየተለዩ በመቃጠል ላይ መሆናቸውም ታውቋል ፡፡ የህዝብ ምሬትና አገዛዙን ከሹመቱ ለማውረድ ህዝብን ነፃ ለማውጣት ያለው መደጋገፍና መረዳት አገዛዙን ግራ ያጋባው ሲሆን አሁን የህዝቡም ቁጣ ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጭ በመሆኑ ህዝቡ ሙሉ በሙሉ አደባባይ ወጥቶ ብርድ ጨለማ ሳይበግረው ስለ ወገኑ ድምፁን በማሰማት ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬ ቀኑን ሙሉ በገብረጉራቻ በነበረው ህዝባዊ አመፅ በርካታ ሰዎች በወታደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸው ታውቋል፡፡ ህዝቡ በወሰደው ጥቃት ከ4 መኪኖች በላይ መቃጠላቸው ታውቋል፡፡የመንግስት ንብረቶች እንዲወድሙም ተደርገዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳና ጎንደር የሚወስደው መንገድም ተዘግቶ ውሏል ፡፡Image may contain: fire and outdoorImage may contain: 10 people, people smiling, crowdImage may contain: one or more people, people standing, fire and outdoor

በተመሳሳይ ደግሞ ተቃውሞ በአርጆ በኢሉባቦር ዞን በሬ ወረዳ በቢሶ ቀበሌ ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን በወያኔ አገዛዝ ሲጨቆን የነበረው ህዝብ ዳውን ዳውን ወያኔ እያለ የተቃሞ ሰልፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ Image may contain: one or more people, people standing, people walking and outdoor
እንዲሁም በጫንጮ ዛሬም የህዝባዊ አመፁ ተቀጣጥሎ ውሏል ፡፡ ዋሊያ ቢራ ተሸክሞ ሲጓዘወ የነበር ከባድ የጭነት መከና ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል በተለያዩ የኦሮሚያ አካባዎች የወያኔ ስርአትን በመቃወም የተለያዩ ተቃሞዎች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡በምስራቅ ወለጋና ጅማ አርጆ ወረዳ ኑኑ ቁምባ በተባለ ቦታ ተቃውሞ ሲደረግ መዋሉ ታውቋል ፡፡
በሰላሌ ቄሮዎችና የክልሉ ፖሊስ በጋራ በመሆን ስርአቱን በመቃወም የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና አገዛዙ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል በቃን በማለት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂዷል ፡፡ በኩዩም ከፍተኛ ተውሞ ተነስቶ በርካታ የስርዓቱ መገልገያ የሆኑ ተሸከርካሪ መኪናዎች መቃጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments:

Post a Comment